በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ በድገሚ የመሬት ንዝረት አጋጠመ
ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ላይ በመተሃራ ያጋጠመው በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ መሆኑ ተነግሯል
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ለ50 ሰከንድ መቆየቱ ታውቋል
በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ የተመገዘበ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ጥቅምት 3 2017 ዓ.ም በበአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በድጋሚ ማጋጠሙ ተነግሯል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ37 አካባቢ ማጋጠሙን እና ለ50 ሰክንድ ያክል መቆየቱን ቮልኖ ዲስከቨሪ የጀርመን ጂኦሳይንስ ማእከልን ዋቢ አድርጎ መረጃ አጋርቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አረጋግጠዋል።
ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት በአዋሽ ፈንታሌ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ተናረዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የመሬት መንቀጥቀጡ ከመሬት በታች 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ የተከሰተ ብሏል ቮልኖ ዲስከቨሪ በበኩሉ።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በመተሃራ ከተማ ላይ መካከለኛ የተባለ ንዝረት እንደነበረውም ነው የተገለጸው።
አዲስ አበባን ጨምሮ በገልምሶ፣ በዴሳ፣ አዳማ፣ ወንጂ እና ደብረ ብህሃንን ከተሞችን ጨምሮ አደጋው ከተከሰተብት እስከ 99 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ባሉ አካባቢዎች መጠነኛ ንዝረት ተሰምቷል።
ባሳለፍነው ሳምንት ምሽት 4 ነጥብ 9 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መተሃራ አካባቢ ማጋጠሙ ይተዋሳል።
መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 2፡10 ላይ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች አነስተኛ የመሬት ንዝረት መስማቱም ይታወሳል።