ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያጋጠማቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢንዶኔዥያ በዓለማችን ብዙ ጊዜ ርዕደ መሬት ያጋጠማት ሀገር ተብላለች
ኢንዶኔዥያ፣ ሜክሲኮ እና ጃፓን ከ900 ጊዜ በላይ ርዕደ መሬት አጋጥሟቸዋል
ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያጋጠማቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ለአጭር ጊዜ ተከስቶ የእድሜ ልክ ጉዳት ከሚያደርሱ የተፈጥሮ ጉዳቶች መካከል አንዱ የሆነው ርዕደ መሬት ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ በየጊዜው በተለያዩ ሀገራት ይከሰታል።
የተወሰኑ ሀገራት ደግሞ ደጋግሞ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች የሚያጋጥማቸው ሲሆን ኢንዶኔዥያ፣ ሜክሲኮ እና ጃፓን በዚህ ይታወቃሉ።
የእስያዋ ኢንዶኔዥያ እስካሁን 1 ሺህ 781 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ያጋጠማት ሲሆን በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿን ህይወት ቀጥፏል።
እንደ ዩኤስ ኒውስ ዘገባ ከሆነ ከኢንዶኔዥያ በመቀጠል ሜክሲኮ 1 ሺህ 497 እንዲሁም ሜክሲኮ 910 ጊዜ የርዕደ መሬት አደጋዎች አጋጥመዋል።
ፊሊፒንስ፣ ቺሊ፣ ቱርክ እና ቻይናም በተደጋጋሚ በርዕደ መሬት አደጋ ከተመቱ የዓለማችን ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።