የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው
በክርስትና እምነት ተከታዮች ከሚከበሩት አበይት በዓላት መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል አንዱ ነው
በዓሉን በማስመልከትም የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች የመልካም በዓል ምኞታቸውን አስተላልፈዋል
የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ተከታዮች ከሚከበሩት አበይት በዓላት መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል አንዱ ነው።
በዓሉን በማስመልከትም የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች የመልካም በዓል ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
የትንሳኤ በአል እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሳኤ የገለጠበት በመሆኑ፤ምእመናንም፤ የተራቡትን በማብላትና፤ የተቸገሩትን በመርዳት በፍቅር ሊያከብሩት እንደሚገባ የሃይማኖት መሪዎች አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ “የክርስቶስ ትንሣኤ ጥላቻንና መጠፋፋትን ያስወገደ፣ ሰላምን ያሰፈነ፣ ዕርቅን ያረጋገጠ ነው” ብለዋል።
“ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ መተባበር ለሁላችንም ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነውና በልዩ ልዩ ምክንያት መከራ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የሚያስፈልጋቸውን በማቅረብ ፋሲካውን አብረናቸው እናከብር” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮዽያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀዻዻሳት ካርዲናል ብጹእ አቡነ ብርሀነ እየሱስ ሱራፌልም፤ እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የገለጠልንን ታላቅ ፍቅር በማሰብ ከክፉ ነገሮች ሁሉ በመራቅ ፍቅርን ተላብሰን መኖር ይገባናል ብለዋል።
የሃይማኖት አባቶች መልዕክታው አክለውም፤ "የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በተግባር በመስራት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ህዝበ ክርስቲያኑም በመላ ሀገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ጥረቱን እንዲያጠናክር የሃይማኖት አባቶቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።