ተዘዋውረን በታዘብናቸው በተወሰኑ የአዲስ አበባ ገበያዎች እንደተለመደው የበዓሉ ገበያ የደራ ነበር
በኮሮና ቫይረስ መከሰት ማግስት የተካሄደው የትንሳኤ በአል ገበያ
ዛሬ የትንሳኤ/ፋሲካ/ በአል ዋዜማ ነው፡፡ ተዘዋውረን በታዘብናቸው በተወሰኑ የአዲስ አበባ ገበያዎች እንደተለመደው የበዓሉ ገበያ የደራ ነበር፡፡
የዶሮ፣የበግና የበሬ ገበያዎች በሻጭና ገዥ ተሞልቶ ተመልክተናል፡፡
ምንምእንኳን ዘንድሮ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት በገበያ ቦታዎች ሰዎቸ አካለዊ እርቀታቸውን እንዲጠብቁ በሃይማኖት ተቋማት ቢገስጹም፤ በመንግስት ቢነገሩም በበዓል ቦታ የተመለከትናቸው ሰዎች ግን ግድ የሰጣቸው አይመስልም፡፡ አልፎ አልፎ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ያደረጉ ሰዎች አሉ፡፡
በገቢያ ቦታዎች ሰዎች እርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገበያዩ ለማድረግ ፖሊሶችም ተሰማርተው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙም ውጤታ የሆኑ አይመስልም፡፡
የበግ ገበያ፤ ለትንሳኤ በአል በግ ገዝቶ በቤት ማረድ ተለምዷል
የዶሮ ገበያ፤ ከፍተኛው እስከ 700 ብር ተሸጧል
የትንሳኤ በአል ላይ በቤት ውስጥ ጨፌ መነስነስ የተለመደ ነው፤ እንደ በአል ማድመቂያ ይጠቀሙበታል፡፡ የበአሉ አክባሪዎችም ከገበያ ገዝተው ይሄዳሉ፡፡
መንግስት የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ለአምስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፤ አዋጁ የተለያዩ እግዶችን ያካተተ ሲሆን ለተግባራዊነታቸውም እየሰራ እንደሆነ እየገለጸ ይገኛል፡፡በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 105 ደርሷል፡፡