በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ክልሎች ከአዲስ አበባ ድንበራቸውን አልፈው ለሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ዝግ አድርገው ቆይተው ነበር፡፡
ክልሎች ድንበራቸውን ዝግ ያደረጉት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ ነበር፤ በወቅቱም የተወሰኑት ክልሎች በቫይረሱ የተገኙ ሰዎቸ ማግኘታቸውን ሪፖረት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ከሰሞኑ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለትንሳዓ በአል እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለመሄድ በተዘጋጁ መንገደኞች መናሀሪያዎች ተጨናንቀው ታዝበናል፡፡
ነገርግን የትራስፖርት ባለስልጣን በዛሬው እለት ባስተለፈው ውሳኔ መሰረት ተቋርጦ የነበረው የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ ተጀምሯል፡፡ በመናሀሪያዎች የሚያስተናግዱ አስተባባሪዎችና ሹፌሮች እንዳረጋገጡልን ከአዲስ አበባ ወደ ክልሎች እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ስድስቱም መናሀሪያዎች ከዛሬ ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አነስተኛና መለስተኛ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ትራንስፖርተሮች ተሽከርካሪዎቻቸውን በማጽዳት ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው መጋቢት 4፣ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ነበር፡፡
ነገርግን ብዙም ሳይቆይ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማና በአማራ ክልል በባህርዳርና በአዊ ዞን አዲስ ቅዳም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በመገኘታቸው ክልሎች የትራንስፖርት እግድ መጣል ጨምሮ በርካታ እርምጃዎችን ወሰዱ፡፡
የፌደራል መንግስት ለአምስት ወር የሚቆይ የአስኳይ ጊዜ ከተጣለ በኃላ የኦሮሚያ የደቡብና የአማራ ክልሎች የታጣትን እግድ አንስተዋል፤የፌደራሉ አዋጅ ወጥ ሆኖ እየተፈጸመ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 92 ደርሷል፡፡