የምዕራብ አፍሪካው ጥምረት ተጠባባቂ ጦሩ ዝግጁ እንዲሆን አዘዘ
ኢኮዋስ በኒጀር በዲሞክራሲ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መውረዳቸው አግባብ ባለመሆኑ ወታደራዊ ጣልቃገብነት አንዱ አማራጭ እንደሆነ ገልጿል
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ምናልባት ወደ ኒጀር ሊገባ ስለሚችል ተጠባባቂ ኃይሉ ዝግጁ እንዲሆን አዟል
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ምናልባት ወደ ኒጀር ሊገባ ስለሚችል ተጠባባቂ ኃይሉ ዝግጁ እንዲሆን አዟል።
ኢኮዋስ በኒጀር በዲሞክራሲ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መውረዳቸው አግባብ ባለመሆኑ ወታደራዊ ጣልቃገብነት አንዱ አማራጭ እንደሆነ ገልጿል።
ኢኮዋስ በኒጀር መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የያዘው አካል ፕሬዝዳንቱን ወደ ስልጣናቸው እንዲመልስ ቀነ ገደብ በማስቀመጥ ቢያስጠነቅቅም፣ ስልጣን የተቆጣጠረው ጁንታ ፍቃደኛ አልሆነም።
የሳህል ቀጣናን የሚያምሰውን እስላማዊ ታጣቂዎችን በመዋጋት ከመፈንቅለ መንግስቱ በፊት የምዕራባውያን አገር በሆነችው ኒጀር ላይ ይደረጋል የተባለው ወታደራዊ ጣልቃገብነት ውጥረት መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት መሀመድ ባዙም ወደ ስልጣን እንዳይመለሱ እክል በሚፈጥሩት ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ የጥምረቱ መሪዎች በናይጀሪያ አቡጃ ስብሰባቸው ተናግረዋል።
የኢኮዋስ ሊቀመንበር የሆኑት የናይጀሪያው ፕሬዝደንት ቦላ ትኑቡ ወታደራዊ ጣልቃገብነትን ጨምሮ ሁሉም አይነት እርምጃዎች እንደመጨረሻ አማራጭ ተይዘዋል ብለዋል።