ማሊ ምርጫ ካላካሄደች ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጣልባት ኢኮዋስ አስጠንቅቋል
የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ(ኢኮዋስ) እስከ ቀጣዩ የካቲት ድረስ ምርጫ እንድታካሂድ አሳሰበ፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ በምርጫ ተመርጠው የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት የነበሩትን ኢብራሂም አቡበከር ኬታ በተፈጸመባቸው መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል፡፡
የ40 ዓመቱ ኮለኔል አስሚ ጎይታ በመሩት መፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ማሊ ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ማሊ ታግዳለች፡፡
ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት እና ለጋሽ ድርጅቶች ከማሊ ወታደራዊ መንግስት ጋር አብረው መስራት ማቆማቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢኮዋስ ጂያን ክላውዶ ብሮ እንዳሉት ማሊ እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ ምራጫ ካላካሄደች ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አስጠንቅቀዋል፡፡
የማሊ ወታደራዊ መንግስት በበኩሉ በፈረንጆቹ እስከ ጥር 2022 ዓመት ድረስ ምርጫ የሚያካሂድበትን መርሃ ግብር እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡ማሊ በፈረንጆቹ ነሀሴ 2020 ዓመት በተካሄደባት መፈንቅለ መንግስት በወታደራዊ የሽግግር መንግስት በመመራት ላይ ትገኛለች፡፡
የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወይም ኢኮዋስ በናይጀሪያ መዲና አቡጃ ባካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ማሊ በ2022 ዓመት ምርጫ እንድታካሂድ አሳስቧል፡፡