ፕሬዘዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቁም እስር የተለቀቁት ከስልጣን ባወረዷቸው ወታደራዊ ባለስልጣናት ነው
የማሊ የቀድሞ ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ባህ ንዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞክታር ቁአኔ ባለፈው በፈረንጆቹ ግንቦት ወር ከስልጣን ባነሷቸው ባለስልጣናት ከቁም እስር ተለቅቀዋል፡፡
የፕሬዘዳንቱንና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ከቁም እስር መለቀቅ ያስታወቀው ከመፈንቅለመንግስት በኋላ ያለውን የሀገሪቱን ሁኔታ የሚቃኘው ኮሜቱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ግንቦት በወታደራዊ ባለስልጣናት የተደረገው እስር ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦባካር ኬታ ላይ ከተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ወዲህ ይህ ሁለተኛው ነው፡፡ በሀገሪቱ የተከሰተው ፖለቲካዊ ምስቅልቅል የቀጣናውንና አጋሮቿንና ፈረንሳይ፤በሀገሪቱ በሚካሄደውም ምርጫ ይመጣል ተብሎ የሚታሰበውን የሲቨል መንግስት ያዘገያል የሚል ስጋት አላቸው፡፡
አለም አቀፉ ማህበረሰብ ፕሬዘዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቁም እስር እንዲፈቱ ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡ የምእራብ አፍሪካ ተወካዮችን ያቀፈው ኮሚቴው፤ መሪዎቹን ከቁም እስር ለመልቀቅ የወሰደውን እርምጃ በበጎ ተቀብለዋል፡፡
ኮሜቴው የማሊን ሽግግር እንደሚደግፍ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ነገርግን የማሊ ባለስልጣናት መልስ አለመስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡