በማእከላዊ ማሊ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 31 ሰዎች ተደገሉ
ጥቃቱ በአካባቢው እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች ሁሉ የከፋ መሆኑ ተገልጿል
በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱና ያልታወቁ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው ቁጥሩ ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል
በማእከላዊ ማሊ ታጣቂዎች ወደ ገበያ የሚሄዱ ሰዎችን አሳፍሮ በነበረ አውቶቡስ ላይ በተተኮሰ ጥይት 31 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ባለስልጣናት ተናግሯል፡፡
ባለስልጣናቱ ጥቃቱ በአከባበው እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች ሁሉ የከፋ እንደሆነ መግለጻቸውንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
በአቅራቢያ የምትገኘውን የባንካስ ከተማ ከንቲባ ሞውላየ ጉይንዶ፤ በአውቶቡሱ ላይ ጥቃት ያደረሱት ታጣቂዎች ማንነት እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል፡፡
“ታጣቂዎች... ተሽከርካሪው ላይ ተኩሰው ጎማውን በሽቷል እንዲሁም ወደ ህዝቡ ተኩሰዋል” ሲሉም ተናግሯል ከንቲባው፡፡
እስካሁን 31 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ፤ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱና ያልታወቁ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው ቁጥሩ ሊያሻቅብ ይችላልም ብሏል፡፡
ከውስጥ ተገኘ ተባለው ደኅንነት መረጃ እንደሚለው ከሆነ ፤ በመኪናው ውስጥ 25 የተቃጠሉ አስከሬኖች ተገኝቷል፡፡በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተሰራጨው ምስልም ቢሆን፤ የመንገደኞች አውቶብሱ በሰው አካል ተሞልቶ ጭስ ሲታይ የሚያሳይ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የምስሎቹን ትክክለኛነት በራሱ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ሮይተርስ አስታውቋል፡፡
በማሊዋ ሞፕቲ ግዘት ውስጥ የሚገኙት መንደሮች ከአልቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለቸው በሚነገርላቸው አማፂያን አማካኝነት በተለያዩ ጊዜያት ጥቃቶች ሲሰነሩባቸው ይስተዋላል፡፡
በአፍሪካ የሳህል አከባቢ ጂሃዲስቶች በተለያ ጊዜያት በሚሰነዝሩት ጥቃት፤ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው እንዲሁም ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የማሊ፣የቡርኪናፋሶ እና ኒጀር ዜጎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡