ኢኮዋስ ከመፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ በጊኒ እና በማሊ ጁንታዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ
ማእቀቡ የፋይናነስና የጉዞ እገዳን እንደሚያካትትም ነው የተገለጸው
ውሳኔው በኢኮዋስ አባል ሀገራት መሪዎች የጸና አቋም ነው ተብሏል
የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በጊኒ እና በማሊ መፈንቅለ መንግስት ባደረጉት ላይ ማዕቀብ ጣለ፡፡
የኢኮዋስ እርምጃ በመፈንቅለ መንግስት በትረ ስልጣን ለጨበጡት ወታደራዊ ኃይሎች ከባድ ምላሽ ነው ተብሎለታል፡፡ኢኮዋስ ከውሳኔ የደረሰው በጊኒ እና ማሊን የተፈጸሙ የመፈንቅለ መንግስታት ድርጊቶች በማስመልከት በጋና አክራ ባከሄደው ስብሰባ ነው፡፡
- የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ጊኒን ከአባልነት አገደ
- “በጊኒ መፈንቅለ መንግስት ከማድረግ ውጭ ምንም አማራጭ አልነበረም”፡-የጊኒ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲያሎ
በዚህም የኢኮዋስ አባል ሀገራት መሪዎች በጊኒ የጁንታ አባላትና ዘመዶቻቸው ላይ ያነጣጠረ የጉዞና ፋይናነስ እገዳ ጥለዋል እንዲሁም በጁንታው ቁጥጥር ስር ያሉት ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ እንዲለቀቁ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡
የኢኮዋስ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጄን ክላውድ ካሲ ብሮው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "በስድስት ወራት ውስጥ ምርጫ መካሄድ አለበት" ብሏል፡፡
ኢኮዋስ፡ በማሊ እንደፈረንጆቹ የካቲት 2022 እንዲደረግ ከስምምነት የተደረሰበትን ምርጫ እውን እንዲሆንና አስቻይ ፍኖተ ካርታ እንደዘጋጅለትም ጫና እየፈጠረ መሆኑን የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ሂደቱን ለማደናቀፍ እየሰሩ ባሉ አካላት ላይ ልክ እንደ ጊኒ ጁንታ አባላት ሁሉ ማእቀብ መጣሉንም ተናግሯል፡፡ ውሳኔው የሁሉም መሪዎች የጸና አቋም እንደሆነም ጭምር ገለጸዋል፡፡
የሰኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል "ዴሞክራሲ፣ሰላምና፣ደህንነት እና መረጋጋን ለመጠበቅ ሲባል የመድረኩ ጠንካራ እርምጃዎች እቀበላለሁኝ " ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አጋርቷል፡፡
የጊኒው ጁንታ ሶሞኑን የሽግግር ሂደት እንዲኖር በሚል ከተለያዩ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ የንግድ ማህበረሰብ እና ፖለቲከኞች ጋር እየመከረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ጁንታው ኢኮዋስን የወከለ ልኡክ ወደ ኮናክሬ መጥቶ ምክክር ያደርጋል ብሎ ሲጠብቅ የነበረ ቢሆነም አለመምጣቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት በትላንትናው እለት ገለጾ ነበር፡፡
ከቅርብ ወራት ጊዜያት ወዲህ በምዕራብ አፍሪካ እየተስተዋለ ያለው ነገር የዴሞክራሲ አቀንቃኞች ነን በሚሉ አካላት ክፉኛ እየተተቸ እና ትኩረት እየተሰጠው ይገኛል፡
አክቲቪስቶች “በምዕራብ አፍሪካ እየተስተዋሉ ያሉ ድርጊቶች ቀጠናው በዴሞክራሲ ያለውን እምነት እየሳሳ መምጣቱንና ለመፈንቅለ መንግስት ትልቅ ቦታ መስጠቱ የሚያመላክት ነው” ብለውታል፡፡
ባለፈው ወርሃ ግንቦት ሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ማሊ መፈንቅለ መንግስትማስተናገዷ የሚታወስ ነው፡፡የማሊ የሽግግር ባለሥልጣናት በመጪው የካቲት ምርጫን ለማደራጀት ቃል ቢገቡም አኳሃናቸው አጥጋቢ እንዳልሆነ ኢኮዋስ ሲወቅስ ቆይቷል፡