በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
ወጣቶቹን ከመሬት ውስጥ ለማስወጣት የተጀመረው ጥረት ከትናንት በስቲያ ተቋርጦ ነበር
በደቡብ ወሎ ደላንታ ወረዳ ኦፓል ለማውጣት በሚል በቁፋሮ ላይ የነበሩ 20 ወጣቶች መሬቱ ከተደረመሰባቸው ስምንት ቀን ሆኗቸዋል
በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋት ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነበር ኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች መውጫ ስፍራ በአለት የተደፈነባቸው፡፡
ህጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው ኦፓል በማውጣት ላይ የነበሩ እነዚህ ወጣቶች ቁጥራቸው 20 ሲሆን ከመሩት በህይወት ለማትረፍ የአካባቢው ማህበረሰብ እስከ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተቋርጦ ነበር።
የደቡብ ወሎ ኮሙንኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እያሱ ዮሀንስ ለአልዐይን እንዳሉት የወጣቶቹን ህይወት ለመታደግ የወረዳው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ እንደነበር ነገር ግን መልክዓ ምድሩ ለቁፋሮ አመቺ አለመሆኑን ተከትሎ ተጨማሪ ሰው ላለማጣት በሚል ቁፋሮው ከአቅም በላይ ነው ተብሎ ቆሞ እንደነበር ተናግረዋል።
ይሁንና የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳድር ለደላንታ ወረዳ ባደረገው የባለሙያ በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ወጣቶቹ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋባቸው ሲሆን በአካባቢው በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀን ጀምሮም ወጣቶቹን ለመታደግ የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ እየቆፈረ ነው የተባለ ሲሆን ወጣቶቹ ያሉት በግምት 750 ሜትር ርቀት ላይ ይሆናልም ተብሏል፡፡
እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ቁፋሮ እንደተቆፈረ የተናገሩት ሀላፊው ቦታው አለታማ እና የቁፋሮ ማሽን ለማስገባት አመቺ አለመሆኑ ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም አክለዋል፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ ኦፓል ማዕድን በማውጣት ስራ ላይ የነበሩ10 ወጣቶች ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሟቸው አራቱ በህይወት መገኘት ችለው ነበር ያሉት አቶ እያሱ በተደረገው ርብርብ ከ11 ቀናት እልህ አስጨራሽ ቁፋሮ በኋላ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ማግኘት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
አቶ እያሱ አክለውም ወጣቶቹን በህይወት ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረው በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ለመታደግ ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡