
53 ቢሊየን ዶላር የሚያስፈልገው እቅዱ ጋዛን በ5 ዓመታት ውስጥ መልሶ መገንባት የሚያስችል ነው
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሀገራቸው ጋዛን መልሶ ለመገንባት ያስችላል በሚል ያዘጋጀችውን እቅድ ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በካይሮ በተዘጋጀ የአረብ ሀገራት አስቸኳይ ጉባዔ ላይ ነው የጋዛ መልሶ ግንባታ እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት።
በእቅዱ መሰረት በመልሶ ግንባታው ፍሊስጤማውያንን ከመሬታቸው ሳያፈናቅል የሚካሄድ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ጋዛን ከሃማስ ውጪ ሌላ ገለልተኛ ኮሚቴ እንዲያስተዳድር ይደረጋልም ብለዋል።
ፕሬዝዳንት አልሲሲ "ጋዛን የሚያስተዳድር ገለልተኛ ኮሚቴ ለማቋቋም ከፍልስጤማውያን ጋር በትብር እየሰራን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
“ግብፅ የጋዛ ሰርጥ ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት የሚወስዱ የፍልስጤም የደህንነት አባላትን በማሰልጠን ላይ ትገኛለች” ሲሉም ገልጸዋል።
ከጋዛ መልሶ ግንባታ ጋር በተያያዘም የግብፅ ትራምፕ "የጋዛ ሪቪዬራ" እቅድ አማራጭ የሆነ እቅድ ይፋ ያደረገች ሲሆን፤ እቅዱ 53 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ እና አምስት አመታትን እንደሚወስድ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ግብጽ ያዘጋጀችው እቅድ ፍልስጤማውያን "በመሬታቸው እንዲቆዩ" የሚያስችል ነው ብለዋል።
በእቅዱ መሰረት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የማገገሚያ ምዕራፍ ሲሆን፤ በዚህም ፍርስራሾችን በማንሳት እና በ3 ቢሊዮን ዶላር ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑን አስታውቀዋል።
የመጀመሪያ ምዕራፍ በትክክል ከሄደ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 200 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን የጋዛ የመገንባት ሂደት ይከናዋነል ብለዋል።
በእቅዱ መሰረት በፈረንጆቹ በ2030 እቅዱ ለ3 ሚሊዮን ሰዎች ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የአውሮፕላን ማረፊያ፣ የኢንዱስትሪ ዞኖች፣ ሆቴሎች እና መናፈሻ ፓርኮች ግንባታ እንደሚጠናቀቅም ተመላክቷል።
ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ በመቀጠልም የአረብ ሀገራት ጋዛን በተመለከተ የግብፅን እቅድ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአረብ ሀገራት አስቸኳይ ጉባዔ ላይ የቀረበው የጋዛ እቅድ ጋዛን የመካከለኛው ምስራቅ ሪቬራ አደርጋለሁ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የሚፎካከር ነው።
ፕሬዝደንት ትራምፕ አሜሪካ ጋዛን በቁጥጥሯ ስር እንደምታደርግ፣ 2.2 ሚሊዮን ገደማ ነዋሪዎቿን ወደ ሌላ ሀገር እንደምታዛውርና "የመካከለኛው ምስራቅ ውብ ቦታ" እንደሚያደርጉ መናገራቸው የአረቡን አለም አበሳጭቷል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ የአረብ ሀገራት በተለይም ግብጽና ጆርዳን 16 ወራት በዘለቀው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት የወደመችው ጋዛ እስከምትጸዳና መልሳ እስከምትገነባ በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን እንዲያስጠልሏቸው ጫና ሲያደርጉ ቆይተወዋል።
ነገርግን የአረብ ሀገራት ትራምፕ ያቀረቡትን ሀሳብ በጽኑ ተቃውመውታል።
የአረብ ሀገራት ፍልስጤማውያን ከቦታቸው ሳይፈናቀሉ የመልሶ ግንባታው አካል መሆን ይጠባቸዋል የሚለውን ሀሳብም ደግፈዋል።