ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ማጠናቀቋን ተከትሎ ግብጽ ምን አለች?
የህዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁትን ኢትዮጵያ አስታውቃለች
ኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ማካሄዷን ተከትሎ ግብጽ ብስጭቷን ገልጻች
የህዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትናትናው እለት በይፋ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል፤ በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ፣ በጉልበታችሁና በጸሎታችሁ በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።
በግድቡ ግንባታ ከውስጥን ከውጭም ጫናዎች እንደነበሩ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎችን በመቋቋም ለዚህ ስኬት ደርሰናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ካሳወቀች በኋላ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ መግለጫ አውጥቷል።
ግብጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጣችው መግለጫ፤ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መቀጥል በ2015 የተፈረመውን የመርህ ስምምነት እና ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ ነው ብላለች።
ኢትዮጵያ በትናንትናው እለት የግዱቡን የውሃ ሙሌት ዙሪያ ያወጣ,ችውን መረጃ አስመልክቶ፤ ኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ማከናወኗ በሶስቱ ሀገራት መካከል በፈረንጆቹ በ2015 የተፈረመውን እና በግድቡ አሞላልና አሰራር ዙሪያ የመርህ ስምምነትን የሚጥስ ነው ብላለች።
ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የተናጠል እርምጃ መውሰድ መቀጠሏ የታችኛውን የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎት ችላ ያለ እና በዓለም አቀፍ ህግ የሚደገፈውን የውሃ ደህንንት ያላገናዘበ ነው ብላለች።
እንዲህ አይነቱ የተናጠል አካሄድና የሚያስከትላቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች በቀጠለው ድርድሮች ላይ ጫና የሚያሳድር መሆኑንም ግብጽ አስታውቃለች።
የሶስቱ ሀገራት የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ድርድር በቅርቡ በግብጽ መዲና ካይሮ ዳግም ሲጀመርም ሀገራቱ በቀጣይ ስለሚያደርጓቸው ድርድሮች፣ የመወያያ አጀንዳዎች እና በሶስቱ ሀገራት ልዩነቶች ዙሪያ መምከራቸው አይዘነጋም።
የሶስቱ ሀገራት የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ቀጣይ ውይይታቸውን በአዲስ አበባ መስከረም ወር ውስጥ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዛቸውም ተገልጿል።
ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ 84 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሀይል በማመንጨት ላይ ናቸው።