ግብጽ ከፈረንጆቹ 1949 ጀምሮ ስምምነቱን የሚያስተዳድረው የምክር ቤት አባል ናት
ከዓለማችን ከፍተኛ ስንዴ አስመጪ ሀገራት አንዷ የሆነችው ግብጽ፤ በሰኔ ወር መጨረሻ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእህል ስምምነት ውል እንደምትወጣ አስታውቃለች።
ይህም ፈራሚዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል ነው የተባለው።
ግብጽ የገበያውን ግልጽነትና የንግድ ትብብር የሚያበረታታ ነው ከተባለው ዓለም አቀፉ የእህል ንግድ ስምምነት መውጣት፤ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተገናኘ በእህል ገበያዎች ውስጥ ውዥንብርን መፈጠሩን ተከትሎ ነው።
ግብፅ ብቸኛው የዓለም አቀፍ የእህል ንግድ ስምምነትን የፈረረመች ሲሆን፤ በፈረንጆቹ ከ1949 ጀምሮ ስምምነቱን የሚያስተዳድረው የምክር ቤት አባል ሆናም ቆይታለች።
ከሰኔ 30፤ 2023 ጀምሮ ለመውጣት ጥያቄ ማቅረቧም ነው የተገለጸው።
ስምምነቱን የሚያስተዳድረው የዓለም አቀፉ የእህል ምክር ቤት ስጋት እንደተፈጠረበት ገልጾ፤ በርካታ አባላት ግብጽ ውሳኔዋን እንድታጤን ይጠይቃሉ ብሏል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሀገሪቱ የምክር ቤት አባልነት ጠብ ያደረገው ነገር የለም ብሏል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሁለት ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ግብጽ የአባልነት ክፍያ ዕዳ አለባት።
በዩክሬን ያለው ጦርነት የግብፅን የስንዴ ግዢ ያስተጓጎለ ሲሆን፤ ካይሮ ከጥቁር ባህር አቅርቦቶች ውጭ እንደ ህንድ ያሉ ሀገራት ላይ እያማተረች ነው ተብሏል።
ጦርነቱ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖም በግብፅ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማባባስ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች መቀዛቀዝ፣ የወደብ ምርቶች መዘግየት እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) የሦስት ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ተቀብላለች።