ግብጽ ያለባት የብድር መጠን 155 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ
በተጠናቀቀው 2022 ዓመት ብቻ የግብጽ ብድር መጠን በ19 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል
የግብጽ ብድር መጠን ከ10 ዓመት በፊት 34 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነበር ተብሏል
ግብጽ ያለባት የብድር መጠን 155 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ።
የሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ያለባት የውጭ እዳ መጠን ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።
እስከ ተጠናቀቀው 2022 ድረስ የካይሮ አጠቃላይ የውጭ እዳ 155 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የምግብ ፍላጎቷን ለመሸፈን ከዩክሬን እና ሩሲያ በስፋት ስታስገባ ለነበረችው ግብጽ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ወጪ እንድታወጣ አድርጓል ተብሏል።
ግብጽ በ2011 ተከስቶ የነበረው ህዝባዊ አብዮት የካይሮ ኢኮኖሚን ወደ ከፋ ጉዳት እንዲገባ አድርጓል የተባለ ሲሆን የዋጋ ግሽበት እና የኮሮና ቫይረስ መከሰት ችግሩን እንዳባባሰውም ተጠቅሷል።
አልዐይን የግብጽ ብሔራዊ ባንክ፣ የገንዘብ ሚንስቴር እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ፈንድ ወይም ከአይኤምኤፍ ባገኘው መረጃዎች መሰረት የግብጽ የውጭ እዳ መጠን 155 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
የብድር መጠኑ ባሳለፍነው 2022 ዓመት ብቻ የ19 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪም አሳይቷል።
የግብጽ ብድር መጠን ከ10 ዓመት በፊት 35 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከአምስት እጥፍ በላይ ጭማሪ እንዳሳየ ተገልጿል።
እንደ ግብጽ ማዕከላዊ ባንክ መረጃ ከሆነ ካይሮ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 84 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመክፈል አቅዳለች።