ግብጽ በፍልስጤም "አሳሳቢ" ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ የአረብ ስብሰባ ጠራች
ይህ ስብሰባ የሚካሄደው ጋዛን ከእስራኤል እንረከባለን የሚለው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር አለምአቀፍ ውግዘት እያስከተለ ባለበት ወቅት ነው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/243-194041-img-20250209-183950-098_700x400.jpg)
ትራምፕ የፈራረሰችው ጋዛ እስከምትገነባ ድረስ ግብጽና ጆርዳን የጋዛ ፍልስጤማውያን እንዲያስጠልሏቸው ጥሪ አቅርበው ነበር
ግብጽ በፍልስጤም "አሳሳቢ" ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ የአረብ ስብሰባ ጠራች።
ግብጽ "አሳሳቢ" ነው ባለችው የፍልስጤም ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚመክር የአረብ ስብሰባ በካቲት ወር የመጨረሻ ሳምንት መጥራቷን የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ ስብሰባ የሚካሄደው ጦርነቱ ሲያበቃ ጋዛን ከእስራኤል እንረከባለን የሚለው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር አለምአቀፍ ውግዘት እያስከተለ ባለበት ወቅት ነው።
ባለፈው ወር ትራምፕ ለ15 ወራት በዘለቀው የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት የፈራረሰችው ጋዛ እስከምትጸዳና እስከምትገነባ ድረስ ግብጽና ጆርዳን የጋዛ ፍልስጤማውያን እንዲያስጠልሏቸው ጥሪ አቅርበው ነበር።
ነገርግን ይህን ሀሳባቸውን ቀይረው አሜሪካ ጋዛን ተቆጣጥራ ማልማት እንደመትፈልግ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ግብጽና ጆርዳንን ጨምሮ በርካታ የአረብ ሀገራት ትራምፕ ያቀረቡትን ፍልስጤማውያን ከጋዛ የማስወጣት ሀሳብ በፍጹም እንደማይቀበሉት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በጻፉት ደብደባ ግልጽ አድርገዋል።
ሀገራቱ ፍልስጤማውያን በመልሶ ግንባታው ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸውና መፈናቀል እንደሌላቸው እንደሚፈልጉ እየገለጹ ናቸው።
በግብጽና ኳታር አደራዳሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድጋፍ አማካኝነት ባለፈው ጥር ወር አጋማሽ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ማስቆም ችሏል።
ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን በጀመረበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሀማስ እና እስራኤል ታጋቾችን በፍልስጤማውያን እረኞች ተለዋውጠዋል።
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር ጥሶ 1200 ሰዎችን ከገደለና 250 ሰዎችን ካገተ በኋላ እስራኤል በወሰደችው መጠነሰፊ ጥቃት ከ47 ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። እስራኤል በጋዛ የዘረ ማጥፋት ፈጽማለች በሚል የቀረበባትን ክስ አስተባብላለች።