የዩክሬን ብርቅ ማዕድናት ምንድን ናቸው?፤ ትራምፕስ ለምን ፈለጓቸው?
ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት አሜሪካ ያደረገችላትን የ300 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ በብርቅ ማዕድናት እንድትከፍላት እንደምትፈልግ ተናግረው ነበር
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/243-162404-img-20250209-152035-306_700x400.jpg)
ዘለንስኪ አሜሪካ ብርቅና ወሳኝ የሚባሉ የዩክሬን ማዕናትን በማውጣት እንድትሰማራ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል
ዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አሜሪካ ብርቅና ወሳኝ የሚባሉ የዩክሬን ማዕናትን በማውጣት እንድትሰማራ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት አሜሪካ ያደረገችላትን የ300 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ በብርቅ ማዕድናት እንድትከፍላት እንደምትፈልግ ተናግረው ነበር። ዘለንስኪ ትራምፕን ጨምሮ ለአጋሮቻቸው ባቀረቡት "የድል እቅዳቸው" ይህን ሀሳብ አንጸባርቀዋል።
እቅዱ የውጭ አጋሮች የዩክሬን ስትራተጂካዊ ማዕድናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚል ይገኝበታል።
አሜሪካ በዩክሬን ብርቅ ማዕድናትና በሌሎች ጉዳዮች ስምምነት ላይ መድረስ እንደምትፈልግ የገለጹት ትራምፕ የማዕድን አይነቶችን በዝርዝር አልጠቀሱም።
ውድ ወይም ብርቅ ማዕድን የሚባለው ኃይልን ወደ እንቅስቃሴ በመቀየር ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ ለሞባይ ስልክና ለሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚያገለግሉ 17 ማዕድናትን ያካተተ ቡድን ነው።
እስካሁን እነዚህን ብረቶች የሚተካ ማዕድን የለም።
እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ከሆነ ኒኬልንና ሊቲየምን ጨምሮ 50 ማዕድናት ለአሜሪካ ኢኮኖሚና ብሔራዊ መከላከያ እጅግ ወሳኝ ተብለው ተለይተዋል።
ዩክሬን በአውሮፓ ህብረት ወሳኝ ከተባሉት 34 ማዕድናት ውስጥ የ22ቱ ክምችት አላት። ይህ ዝርዝር የኢንዱስትሪና የግንባታ ግብአቶችን፣ ፌሮአሎይ፣ ውድ ብረቶችን እና ጥቂት ብርቅ የመሬት ማዕድናትን ያካትታል።
ዩክሬን በቂ የሚባል የድንጋይ ከሰል ክምችት ያላት ቢሆን አብዛኞቹ ቦታዎች አሀኑን ላይ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ናቸው።
የዩክሬን ብርቅ ማዕድናትና አገልግሎታቸው
የአውሮፓ የዳቦ ቅርጫት በመባል የምትታወቀው ዩክሬን የብዙ ውድ ማዕድናት ክምችት ባለቤት ነች። ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ ለመከላከያ፣ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ለሚጠቀሙ ኩባንያዎች፣ ለኤየሮስፔስና አረንጓዴ ኃይል ወሳኝ ናቸው።
እንደ ጂኦሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ ከሆነ ዩክሬን ለቴሌቪዥንና ለመብራት የሚጠቅም እንደላንታነምና ሴሪየም ያሉ እንዲሁም ለንፋስ ኃይል ተርባይንና ለኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ የሚያገለግል ኒዮዲሚየም ማዕድን ክምችት ባለቤት ነች። ከዚህ በተጨማ ሀገሪቱ ለላስርና ለኑክሌር ኃይል የሚውሉት ኢብሪየምና ይትሪየም በሰፊው ይገኙባታል። በአውሮፓ ህብረት የተጠና ጥናት እንደሚያሳየው ሀገሪቱ የስካንዲየም ማዕድን አላት።
ዘለንስኪ ባለፈው አረብ እለት በሰጡት ቃለ ምልልስ ሩሲያ ዩክሬን ግማሽ ያህሉ ብርቅ ማዕድን ያለበትን ቦታ ይዛለች። የማዕድን ዘርፍ ባለሙያዎች እንዳሉት ዩክሬን ብርቅ ማዕድናቷን ለገበያ አላቀረበችም።
ዘለንስኪ ዩክሬን በአውሮፓ የቲታኒየምና የዩራኒየም ከፍተኛ ክምችት ያላት ሀገር ነች ብለዋል። የሀገሪቱ የጂኦሎካል አገልግሎት መረጃ እንደሚያመለክተው ዩክሬን ለባትሪ፣ ለሴራሚክና ለመስተዋት መስሪያ ሚያገልግል የተረጋገጠ 500ሺ ሜትሪክ ቶን ሊቲየም አላት። ለኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መስሪያ እንደግባአት የሚያገለግለው ግራፋይት 20 በመቶ የሚሆነው ክምችት የሚገኘው በዩክሬን ነው። ጠንካራ ለሆነው የብረት ኢንዱስትሪያዊ የሚያገለግል የድንጋይ ከሰል ክምችቷ በምስራቅ ተከማችቶ የነበረ ሲሆን አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ሆኗል። አሁን ላይ 40 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ የብረት ሀብት በሩሲያ ቁጥጥር ስር መግባቱን "ዊ በመውል ዩክሬን" የተባለው ቡድን መረዳ ያመለክታል።