የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኮሪደር ለቆ እየወጣ ነው ሲል ሀማስ አስታወቀ
የኮሪደሩ በእስራኤል መዘጋት በደቡብ ጋዛ ያሉ ማህበረሰቦች በሰሜን ካሉት ጋር እንዳይገናኙ አድርጎ ነበር
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/243-175805-img-20250209-165442-154_700x400.jpg)
የእስራኤል ጦር ከቀጣናው መውጣት ሀማስና እስራኤል በደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የሚጠበቅ እርምጃ ነው ተብሏል
የእስራኤል ጦር ናዛሪም እየተባለ ከሚጠራው በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኮሪደር ለቆ እየወጣ ነው ሲል ሀማስ በዛሬው እለት አስታውቋል።
የእስራኤል ጦር ከቀጣናው መውጣት ሀማስና እስራኤል በደረሱት የመጀመሪያ ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የሚጠበቅ እርምጃ ነው ተብሏል።
ሮይተርስ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የእስራኤል ምንጭን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ጋዛ ከነበረው ይዞታ እየወጣ ነው።በቦታው ያለው የእስራኤል ጦር ቁጥር ቀደም ሲል ነበር የቀነሰው።
ሀማስ የእስራኤል ኃይሎችን ከቦታው መውጣት እንደ ድል ቆጥሮ እያከበረው ሲሆን በኮሪደሩ የሚያቋርጡ ፍልስጤማውያንን ለመቆጣጠር ሀማስ የራሱን ፖሊስ ወደ ቦታው ልኳል።
ሮይተርስ የእስራኤል ጦር ከቦታው ሲወጣ የሚያሳይ ቪዲዮ እንደደረሰው ገልጿል።
የኮሪደሩ በእስራኤል መዘጋት በደቡብ ጋዛ ያሉ ማህበረሰቦች በሰሜን ካሉት ጋር እንዳይገናኙ አድርጎ ነበር።
የእስራአል ኃይለች ጦርነቱ ከተጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ጀምሮ ከእስራኤል ድንበር እስከ ሜዲትራኒያን ባህር ድረስ የሚሸፍነውን አራት ማይል ቦታ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ቆይተዋል።
የኮሪደሩን መከፈት ተከትሎ በጦርነቱ ወቅት ተፈናቅለው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜን ጋዛ ጎርፈዋል። ጥቂቶች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባዩት ነገር ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል።
እስራኤል ያካሄደችውን መጠነሰፊ ጥቃት ተከትሎ አብዛኛው የጋዛ ክፍል ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል። ቤታቸው ፈርሶ ያገኙት የተወሰኑ ፍልስጤማውያን ወደ መጡበት ደቡባዊ ጋዛ ተመልሰዋል።
በግብጽና ኳታር አደራዳሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድጋፍ አማካኝነት ባለፈው ጥር ወር አጋማሽ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ማስቆም ችሏል።
ስምምነት ተግባራዊ መሆን በጀመረበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሀማስ እና እስራኤል ታጋቾችን በፍልስጤማውያን እረኞች ተለዋውጠዋል።