ታግተው የነበሩ እስራኤላውያን ሞተው መገኘታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ከባድ እና ያልተጠበቀ ጥቃት አደርሶ 240 ሰዎች አግቶ መውሰዱ ይታወሳል
የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋሪ እንዴት እንደሞቱ ለማወቅ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል
ታግተው የነበሩ እስራኤላውያን ሞተው መገኘታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።
በሀማስ እጅ የተገደሉ አምስት እስራኤላውያን ታጋቾች በጋዛ ስርጥ በሚገኘው የመሬት ውስጥ ዋሻ መገኘታቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋሪ እንዴት እንደሞቱ ለማወቅ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ የሟቾችን ማንነት ለቤተሰቦቻቸው ይነገራል ብለዋል።
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ከባድ እና ያልተጠበቀ ጥቃት አደርሶ ሶስት ወታደሮችን ጨምሮ 240 ሰዎች አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።
ጥቃቱን ተከትሎ እስራኤል በአየር እና በእግረኛ ጦር የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍታለች፤ አሁንም እያጠቃች ነው።
የታጋች ቤተሰቦች ድርድር ተደርጎ የታገቱት እንዲለቀቁ ጥያቄዎች ቢያቀርቡም፣ ሀማስን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል ጥቃቷን ቀጠለች።
እስራኤል በእግረኛ ጦር ጋዛ ከገባች በኋላ የሀማስ ዋና መቀመጫ በሆነችው ኳታር አደራዳሪነት ለከታታይ ሰባት ቀን ተኩስ አቁም ስምምነት ተደረሰ።
የተኩስ አቁሙ በቆየበት ጊዜ ሀማስ ካገታቸው ውስጥ 50 የሚሆኑ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤልም ያሰረቻቸውን በርካታ ፍልስጤማውያን ለቀቀች።
ሰባት የቆየው ተኩስ አቁም መራዘም አልቻለም።
ስምምነቱ ከፈረሰ በኋላ ጦርነቱ በድጋሚ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
በእስራኤል ጥቃት እስካሁን ከ20ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።