ግብጽ ከጦርነት በኋላ ስለሚኖረው አስተዳደር ላይ ከማተኮር ይልቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጻለች
ግብጽ ውድቅ ያደረገችው የእስራኤል ጥያቄ ምንድነው?
እስራኤል በጋዛ ያለውን ከጦርነት ነጻ ቀጣና ወይም በፈር ዞን ለመቆጣጠር ያቀረበችውን ጥያቄ ግብጽ ውድቅ ማድረጓን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ ሶስት የጸጥታ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግብጽ፣ እስራኤል በግብጽ-ጋዛ ድንበር መካከል ያለውን በፈር ዞን ለመቆጣጠር ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋዋለች።
ግብጽ ከጦርነት በኋላ ስለሚኖረው አስተዳደር ላይ ከማተኮር ይልቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጻለች።
በእስራኤል የተከበበችው ጋዛ 13 ኪሎሜትር የሚረዝም ድንበር ከግብጽ ጋር ትጋራለች።
ግብጽ ከኳታር ጋር በመሆን በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ የመሪነት ሚና ተጫውታለች።
የግብጽ ምንጮች እንደገለጹት በእነዚህ ንግግሮች ወቅት እስራኤል ተጨማሪ ጥቃትን ለመከላከል በድንበር አካባቢ ያለውን ጠባብ የፊላደልፊ ኮሪዶር ለመቆጣጠር ጠይቃ ነበር።
ሀማስ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል እስካሁን በወሰደችው የአጸፋ ጥቃት 23ሺ ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገልጿል።
የእስራኤል ባለስልጣንም የፊላደልፊ መተላለፊያን ከግብጽ ጋር በጋራ የመቆጣጠር ጉዳይ መነሳቱን ተናግረዋል።
ነገርግን ባለሴልጣኑ ግብጽ ስለመቃወሟ መረጃ የለኝም ብለዋል።
ሮይተርስ ለግብጽ መንግስት ቅርበት ያለውን አል ቋሄራ ዜናን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ መተላለፊያውን ለመቆጣጠር ግብጽ እና እስራኤል ሊተባበሩ ነው የሚለው ሪፖርት ሀሰት ነው ብሏል።
የግብጽ ምንጮች እንደገለጹት አሁን እየተካሄደ ባለው የተኩስ አቁም ንግግር ላይ የእስራኤል ባለስልጣናት ስለመቆጣጠር አለማውራታቸውን፣ ነገር ግን ቦታው በጋራ መቃኘት እንደሚፈል ገልጸዋል።
የግብጽ አደራዳሪዎች ግን ሀሳቡን ውድቅ አደርገውታል።
ግብጽ በቦታው ያለውን የድንበር አጥር እየጠናከረች ነው ተብሏል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የግብጽ እና ጋዛ ድንበርን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።