ቱርክ ከእስራኤሉ ሞሳድ ጋር በመገናኘት የጠረጠረቻቸውን 15 ሰዎች አሰረች
ቱርክ ከአብዛኛው ምዕራባውያን ሀገራት እና ከተወሰኑ የአረብ ሀገራት በተለየ መልኩ ሀማስን በሽብርተኝነት አልፈረጀችም
የቱርክ ባለስልጣናት እስራኤል ከፍልሴጤም ግዛት ውጭ የሚኖሩ የሀማስ አባላትን ለማሳደድ የምትሞክር ከሆነ ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቀው ነበር
ቱርክ ከእስራኤሉ ሞሳድ ጋር በመገናኘት የጠረጠረቻቸውን 15 ሰዎች አሰረች።
የቱርክ ፍርድ ቤት ከእስራኤሉ ሞሳድ የሴላላ ድርድት ጋር ግንኙነት በማድረግ እና በቱርክ የሚኖሩ ፍልሴጤማውያን ለማጥቃት በማቀድ የተጠረጠሩ 15 ሰዎች እንዲታሰሩ እና ሌሎች ሰምንት ሰዎች ደግሞ እንዲባረሩ ትናንት መወሰኑን ሮይተርስ የቱርኩን ቲአርቲ ሀበር ጠቅሶ ዘግቧል።
የቱርክ ባለስልጣናት እስራኤል ከፍልሴጤም ግዛት ውጭ የሚኖሩ የሀማስ አባላትን ለማሳደድ የምትሞክር ከሆነ ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን ካስጠነቀቁ በኋላ በዚህ ሳምነት መጀመሪያ ላይ 34 ሰዎችን አስረዋል።
መጀመሪያ ታስረው የነበሩት 11 ሰዎች ምን እንደተወሰነባቸው ዝርዝር መረጃ አልወጣም።
ቱርክ ከአብዛኛው ምዕራባውያን ሀገራት እና ከተወሰኑ የአረብ ሀገራት በተለየ መልኩ ሀማስን በሽብርተኝነት አልፈረጀችም።
የቱርክ ኤምአይቲ ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ እና የኢስታንቡል ጠበቃ የጸረ-ሽብር ቢሮ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ በስምንት ግዛቶች ያሉ ቦታዎችን አላማ አድርጎ ነበር።
ቱርክ፣ እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በጽኑ ተቃውማለች።
የቱርኩ ፕሬዝደነትት ኢርዶጋን እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ባለው ወንጀል በአለምአቀፉ ፍርድ ቤት መከሰስ አለባት ማለታቸው ይታወሳል።