አል አህሊይ ካይዘር ቺፍስን 3ለ0 በሆነ ውጤት በመርታት የዋንጫው ባለቤት መሆን ችሏል
የግብፁ አል አህሊይ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ትናት ምሽት ለ10ኛ ጊዜ በማንሳት የክብረወሰን ባለቤት መሆን ችሏል።
የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በትናትናው እልት ምሽት የግብፁን አል አህሊይ ከደቡብ አፍሪካው ካይዘር ቺፍስ ጋር አገናኝቷል።
ትናንት ምሽት በሞሮኮ የተደረገውን ፍጻሜ ጨዋታም አል አህሊይ ካይዘር ቺፍስን 3ለ0 በሆነ ውጤት በመርታ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችሏል።
በጨዋታውም ሞሃመድ ሸሪፍ በ53ኛ ደቂቃ፣ መሃመድ ማግዲ አፍሻ በ64ኛው ደቂቃ እንዲሁም አሚር ኤል ሶሊያ በ74ኛው ደቂቃ አል አህሊይን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
ይህንን ተከትሎም የግብፁ አል አህሊይ የእግር ኳስ ክለብ የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳት ችሏል።
አል አህሊይ የትናንት ምሽቱን ጨምሮ ክለብ የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ለ10ኛ ጊዜ ማነሳት መቻሉም ታውቋል።
ይህም በአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫ ታሪክ ዋንጫውን 10 ጊዜ ያነሳ ብቸኛው በመሆን አል አህሊይ ዋንጫውን ብዙ ጊዜ በማሳት ባለ ክብረወሰን መሆን ችሏል።
የግብፁ ዛማሌክ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ቲፒ ማዜንቤ የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን እያንዳንዳቸው 5 ጊዜ በማንሳት አል አህሊይን ይከተላሉ።