ኢትዮጵያና ኤርትራ በሴካፋ እግርኳስ መክፈቻ ውድድር 3-3 አቻ ተለያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው አለመግባባት ተፈትቷል
ሁለቱ ሀገራት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ውድድር ሲያካሂዱ ከ28 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
ከ23 አመት በታች የሆኑ የኢትዮጵያ የኤርትራ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ41ኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫ ውድድር የመክፈቻ ውድድር በባህርዳር አለምአቀፍ ስቴዲየም ጀምረዋል፡፡
ጨዋታውን በኮሮና ቫይረስ ምክንት ተመልኳቾች ወደ ስቴዲየም ገብተው መመልከት አልቻሉም፡፡
የውድድሩ መክፈቻ ስነስርዓትን በአሁኑ ሰዓት የተጀመረ ሲሆን፤ የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴድየም በእግር ኳስ ታዳሚዎቸ ደምቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ በጨዋታው የሚጠቀሙት የመጀመርያ አሰላለፍም ታውቋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ የግብ ጠበቂ ፅዮን መርዕድ ከግብ ብረቶቹ መካከል ሲቆም ኃይሌ ገብረትንሳኤ፣ መናፍ ዐወል፣ ሠለሞን ወዴሳ እና ረመዳን የሱፍ የቡድኑ አራት ተከላካዮች ሆነዋል።
መሐል ሜዳ ላይ ሀብታሙ ተከስተ፣ አብዱልሃፊዝ ቶፊቅ እና ዊልያን ሠለሞን ተጣምረዋል። የቡድኑን የፊት መስመር ደግሞ ቸርነት ጉግሳ፣ ሙኧዲን ሙሳ እና አቡበከር ናስር እንደሚመሩት ይሆናል።
በኢትዮጵያና በኤርትራ መከካል የሚካሄድው የብሄራዊ ቡድን ስፖርታዊ ውድድር፤በሁለቱ ሀገራት መካከል ለ30 አመታት የሚጠጋው አለመግባባት ከተፈታ በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ፖለቲካዊ አለመግባባት መፍታት የቻለችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ መሆኑ ይታወሳል፡፡