አሜሪካ በሰብአዊ ጥሰት ምክንያት ለግብጽ ልትስጠው የነበረውን 130 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ማገዷን ገለጸች
ብሊንከን ግብጽ የፖለቲካ እስረኞችን በመልቀቅ መሻሻል አሳይታለች ብለዋል
የመብት ተሟጋቾች ለግብጽ ሊሰጥ የታሰበው እርዳታ ሙሉ በሙሉ እንዳይለቀቅ ጫና በማድረግ ላይ ናቸው
የጆ ባይደን አስተዳደር ግብጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን ባለማሟላቷ ምክንያት ሊሰጣት ከነበረው ውስጥ 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንዲታገድ መደረጉን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ግብጽ በፖለቲካ እስር ላይ ማሻሻያዎችን እያደረገች ስለሆነ የተወሰነ እርዳታ እንደሚለቀቅላት ባለስልጣኑ መናራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን ግብጽ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኖችን በመልቀቋ መሻሻሎችን አሳይታለች ብለዋል፡፡
የመብት ተማጋቾች ግን ለግብጽ ሊሰጥ የታሰበው 300 ሚሊዮን ዶላሩ እንዳይለቀቅላት ጫና በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ነገር ግን አስተዳደሩ ሙሉውን የ300 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ እንዲያግድ የጠየቁት የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ውሳኔው አሜሪከ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር ለገባችው ቁርጠኝነት “ክህደት” ነው ሲሉ ቅር እንዳሰኛቸው ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኢሜል በላከው መግለጫ “በግብፅ ስላለው የሰብአዊ መብቶች አሳሳቢ ጉዳዮች መወያየታችንን ቀጥለናል” ብለዋል።
ሚኒስትር ብሊንከን የግብፅ መንግስት የተወሰኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን በአስተማማኝ ሁኔታ ከፈታ 130 ሚሊዮን ዶላር በመጠቀም ወደፊት ይሄዳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡