የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ
የግብጽ መከላከያ ቃል አቀባይ የአውሮፕላኑ የተከሰከሰበትን ቦታ ግልጽ አላደረጉም
የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላን በልምምድ ላይ እያለ ተከሰከሰ
በግብጽ የጦር አውሮፕላን በልምምድ ላይ እያለ መከስከሱ ተገለጸ፡፡
የአውሮፕላን አብራሪውን ጨምሮ በልምምዱ ላይ የነበሩ ሌሎች ሰዎች ከአደጋው ተርፈዋል ተብሏል፡፡
የግብጽ መከላከያ ቃል አቀባይ ኮለኔል ጋሪብ አብደል ህፊዝ እንዳሉት ወታደራዊ አውሮፕላኑ በትናንትናው ዕለት በልምምድ ላይ እያለ መከስከሱን ተናግረዋል፡፡
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ አውሮፕላኑ የተለመደውን የአየር ሀይል ልምምድ በማድረግ ላይ ሳለ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ተከስክሷል ብለዋል፡፡
በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩት ሰዎች ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም ያሉት ቃል አቀባዩ ጉዳዩን ለማጣራት አስፈላጊው ምርምራ በሚመለከተው አካል እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይሁንና ቃል አቀባዩ በልምምድ ላይ የነበረው አውሮፕላን ምንነት እና የተከሰከሰበትን ቦታ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡