ግብጽ የቀይ ባህር ዳርቻ መዝናኛ ቦታዎችን ዘጋች
ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ሁለት የውጭ ሀገራት ዜጎች በሻርክ መበላታቸውን ተከትሎ ነው
የሻርኩ ጥቃት በግብጽ ቱሪዝም ላይ ስጋትን ደቅኗል
ግብጽ የሻርክ ጥቃትን ተከትሎ በቀይ ባህር ዳርቻ የሚገኙ መዝናኛዎችን ዘግታለች።
ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ የቀይ ባህር መዝናኛ የባህር ዳርቻዎች በጎብኚዎች እንዳይታዩ ዘግታለች፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ግብጽ ከዚህ ውሳኔ ለይ የደረሰችው ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በሻርክ መጠቃታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የ68 ዓመቷ አውስትራሊያዊ ባሳለፍነው አርብ ዕለት በቀይ ባህር መዝናኛ ላይ እየዋኘች እያለች በሻርክ ተጠቅታ ህይወቷ ማለፉን የግብጽ ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡
በቀይ ባህር ለይ የሻርክ ጥቃት ያልተለመደ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዚህ ገዳይ እንስሳ የሚጠቁ ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተጠቅሷል፡፡
የአሁኑ የሻርክ አደጋ በኮሮና ቫይረስ ተጎድቶ ለነበረው የግብጽ ቱሪዝም ስራዎች ላይ ስጋትን እንደፈጠረ የሐገሪቱ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ተጨማሪ ጥናት እስከሚካሄድ ድረስ የቀይ ባህር መዝናኛ ስፍራዎች በጊዜያዊነት ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑ ጠቅሷል፡፡
በፈረንጆቹ 2018 ላይ በአንድ የቸክ ሪፐብሊክ ዜግነት ባላት ጎብኚ ላይ በዚሁ በቀይ ባህር መዝና ኛ ስፍራዎች ላይ እየዋኘች ባለችበት ወቅት በሻርክ ተጠቅታ ህወቷ ማለፉ ይታወሳል፡፡
እንዲሁም በፈረንጆቹ 2010 ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ አምስት የሻርክ ጥቃቶች ተፈጽመው አራት ሰዎች አካላዊ ጉዳት ሲያጋጥማቸው አንድ ጀርመናዊ ጎብኚ ደግሞ በደረሰበት ጥቃት ህይወቱ አልፏል፡፡