ለዓለም ብርቅ የሆኑት የኬንያ ነጭ ቀጭኔዎች በአዳኞች ተገደሉ
ለዓለም ብርቅ የሆኑት የኬንያ ነጭ ቀጭኔዎች በአዳኞች ተገደሉ
በዓለም ላይ ብርቅዬዎቹ የኬንያ ነጭ ቀጭኔዎች በአዳኞች መገደላቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ ሁለቱ ቀጭኔዎች ተገድለው የተገኙት በኬንያ የዱር እንስሳት ማቆያ ስኬለታል በተባለ ግዛት መሆኑን የእሻቅብኒ ሂሮላ ጥብቅ ቦታ ጥበቃዎች ገልጸዋል፡፡
ቀጭኔዎቹ ከእይታ ጠፉ የሚል ሪፖርት ከደረሰው በኋላ የኬንያ የዱር እንሰሳት አገልግሎት ለእንሰሳት ማቆያ ማእከል ደውሏል፡፡ የዱር እንሰሳት ባለስልጣናት የቀጭኔዎቹን አጥንት ካገኙ በኋላ ከአራት ወራት በፊት ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ተናግረዋል፡፡
የጥበቃ ቦታው ስራ አስኪያጅ ሞሀመድ አህመድኑር “ይህ ቀን በተለይ ለእጃራ ማህበረሰብ እንዲሁም ለኬንያ የሀዘን ቀን ነው፤ እኛ በዓለም ላይ ብቸኛ የነጭ ቀጭኔዎች ጠባቂ የሆንን ማህበረሰብ ነበርን”ብለዋል፡፡
የአካባቢው ማህበረሰብ ለጥበቃ በሚል ያደረጋቸውን ትላልቅ ጥረቶች ችግር ውስጥ የሚጥል ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ ድርጊቱ ጥበቃውን አጠናክሮ ለመቀጠልም ማንቂያ ደውል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኬንያ የዱር እንሰሳት አገልግሎት እንዴት እንተገደሉ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የመጀመሪያዋ ነጭ ቀጭኔ እ.ኤ.አ. በ2017 ስትገኝ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንን ቀልብ መሳብ ችላ ነበር፡፡ በህገወጥ ዝውውርና በአደን ምክንያት የዓለም ረጅም እንሰሳት የሆኑት ቀጭኔዎች በ30 ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ 40 በመቶ ቁጥራቸው መቀነሱን የአፍሪካ የዱር እንሰሳት ፋውንዴሽን ይገምታል፡፡