
ባለፈው እሁድ የተጀመረው ምርጫ በህዝብ የተመረጡት የቀድሞው ፕሬዝደንት መሀመድ ሙርሲ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ለአል ሲሲ ሶስኛቸው ነው
የግብጹ ፕሬዝደንት አል ሲሲ ምርጫውን ለማሸነፍ እየተንደረደሩ መሆኑ ተገለጸ።
አል ሲሲ በከፍተኛ ድምጽ ያሸንፋሉ ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ፣ ግብጻዊያን መራጮች ለሶስተኛ ጊዜ እና ለመጨመረሻ ቀን ድምጽ እየሰጡ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
አል ሲሲ ትክክለኛ ውድድር በሌለበት ምርጫ ለተጨማሪ ስድስት አመት ስልጣን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሚዲያዎች ዜጎች እንዲመርጡ ከፍተኛ ቅስቀሳ ቢያደርጉም፣ ድምጽ መስጠታቸው ለውጥ እንደማያመጣ የሚገልጹት ብዙ ግብጻውያን ፍላጎት የላቸውም።
ባለፈው እሁድ የተጀመረው ምርጫ በህዝብ የተመረጡት የቀድሞው ፕሬዝደንት መሀመድ ሙርሲ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ለአል ሲሲ ሶስኛቸው ነው።
ግብጹን ለረጅም ጊዜ የመሩት ሁስኒ ሙባረክ በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከተነሱ ከአመት በኋላ ነበር ሙርሲ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጥ የቻሉት።
ከሙርሲ መወገድ በኋላ ስልጣን የያዙት አል ሲሲ በሺዎች የሚቆጠሩ የሙርሲ ደጋፊዎችን በማስር እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ጭቆና በማድረግ በአለምአቀፍ ተቋማት ትችት ይቀርብባቸዋል።
በዚህ ምርጫ ብዙም የማይታወቁ ሶስት ተቃዋሚዎች እየተሳተፉ ናቸው።
በጣም ታዋቂ የነበረው እና ምናልባትም ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ፖለቲከኛ፣ ባለስልጣናት እና ወሮበሎች ደጋፊዎቹን ኢላማ እያደረጉበት እንደሆነ በመግለጽ ነበር ባለፈው ጥቅምት ወር እንደማይወዳደር ያስታወቀው።
ነገርግን የብሔራዊ የምርጫ ባለስልጣን ይህን ክስ አይቀበልም።
ተችዎች ምርጫው ለይስሙላ የሚካሄድ ነው ይላሉ።
መንግስት የተነሳበትን ትችት ለመመለስ ብሔራዊ የንግግር መድረክ አመቻችቷል፤ተዋቂ እስረኞችን ከእስር ፍትቷል።
አል ሲሲ ሰላም እና ጸጥታ ወሳኝ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።
ግብጹ በአሁኑ ወቅት በድንበሯ በጋዛ እና በሱዳን በኩል ሁለት ጦርነቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ።