የግብጹ ፕሬዝደንት አልሲሲ ከሶሪያ መሪ አልሻራ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በካይሮ ተገናኙ
አልሻራ አማጺ ኃይሎችን በመምራት የበሽር አላሳድ መንግስትን ከገረሰሰ ወዲህ ከምዕራባውያንና ከአረብ ሀገራት ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ ነው

የግብጽ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ሲሲ ከአል-ሻራ ጋር በነበራቸው ውይይት በሶሪያ የትኛውም የፖለቲካ ኃይል ያላገለለ አጠቃላይ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር ማሳሰባቸውን ገልጿል
የግብጹ ፕሬዝደንት አቡድል ፈታህ አል ሲሲ በትናንትናው እለት በካይሮ በጋዛ መልሶ ግንባታ ላይ ለመምከር ከተዘጋጀው ጉባኤ ጎን ለጎን ከአዲሱ የሶሪያ መሪ አህመደ አል-ሻራ ጋር ተገናኝተዋል።
አልሻራ አማጺ ኃይሎችን በመምራት ባለፈው ታህሳስ ወር ለ24 አመታት ሶሪያን ያስተዳደራትን የበሽር አላሳድ መንግስትን ከገረሰሰ ወዲህ ከምዕራባውያንና ከአረብ ሀገራት ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ ነው።
በመካከለኛው ምስራቅ ትልቅ ተጽዕኖ ያላቸውና የአሜሪካ አጋር የሆኑት ሲሲ ብዙ ህዝብ ባለባት የአረብ ሀገር በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ከፍተው ቆይተዋል።
ካይሮ ከሎሎች የአረብ ሀገራት በተለየ መልኩ አዲሱን የሶሪያ መንግስት በጥንቃቄ ነው የምታየው።
ሮይተርስ የሶሪያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ እንደዘገበው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ ሀሰን አልሽባኒ መሳተፋቸውን ጠቅሷል።
የግብጽ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ሲሲ ከአል-ሻራ ጋር በነበራቸው ውይይት በሶሪያ የትኛውም የፖለቲካ ኃይል ያላገለለ አጠቃላይ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር ማሳሰባቸውን ገልጿል። ሲሲ አክለውም ግብጽ የሶሪያውያን አንድነትና መሬት እንዲጠበቅ እንደምትፈልግና በሶሪያ ግዛት ላይ የሚደረግን ማንኛውንም ጥቃት እንደማትቀበል ገልጸዋል።