ግብጽ ጥያቄዋ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ ውድድሩን በማዘጋጀት የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች
ግብጽ በ2036 የበጋ ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ጥያቄ እንደምታቀርብ የግብፅ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ አስታውቋል፡፡
ግብጽ የጠማስተናገድ ጥያቄዋ የሚሳካላት ከሆነ ውድድሩን በማዘጋጀት የመጀመሪያዋ የአረብ ወይም የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች ብለዋል።
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ለማመልከት ፍላጎት እንዳላቸው ሚኒስትር አሽራፍ ሶቢ በካይሮ ለአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባች አቀባበል ባደረጉበት ወቅት መናራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ባች የተባለው የግብፅ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ የግብፅ የስፖርት መሠረተ ልማት ዝግጅቱን ማስተናገድ የሚችል ነው ብሏል።
የበጋው ኦሊምፒክ በ 2024 በፓሪስ ፣ በፈረንጆቹ 2028 ሎስ አንጀለስ እና በ 2032 በብሪስቤን ፣ አውስትራሊያ ይከተላሉ ።
የ2036 ኦሎምፒክን ለማስተናገድ የማመልከቻው ሂደት ገና ያልጀመረ ሲሆን ጀርመን፣ ሜክሲኮ፣ ቱርክ፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ኳታርን ጨምሮ ሀገራት ፍላጎት እንዳላቸው መረጃዎች ወጥተዋል፡፡