ፖለቲካ
ግብጽና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ወደ አምባሳደር ደረጃ ከፍ አደረጉ
የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝደንቶች በሰኔ ወር መጨረሻ ባደረጉት የስልክ ንግግር የዲፕሎሚሲ ግንኙነታቸውን ከፍ ለማድረግ ተስማምተው ነበር
ባለፉት አመታት ካይሮ እና አንካራ በፈረንጆቹ 2013 የሻከረውን ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ የሚኒስትሮች ስብሰባ ሲያደርጉ ቆይተዋል
የሁለቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ እንደገለጹት ግብጽ እና ቱርክ በመካከላቸው ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ውክልና ወደ አምባሳደር ደረጃ ከፍ ለማሳደግ ወስነዋል።
የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝደንቶች በሰኔ ወር መጨረሻ ባደረጉት የስልክ ንግግር የዲፕሎሚሲ ግንኙነታቸውን ከፍ ለማድረግ ተስማምተው ነበር።
ሀገራቱ ግንኙነቱን ከፍ ያደረጉት ፕሬዝደንቶቹ በተነጋገሩት መሰረት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ቱርክ፣ ሳሊህ ሙትሉን በካይሮ የቱርክ አምባሳደር አድርጋ ስትሾም፣ ግብጽ ደግሞ አሚር ኢልሃሚን በአንካራ የግብጽ አምባሳደር አድርጋ ሾማለች።
ባለፉት አመታት ካይሮ እና አንካራ በፈረንጆቹ 2013 የሻከረውን ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ የሚኒስትሮች ስብሰባ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ግብጹ፣ ቱርክ ለሙስሊም ብራዘርሁድ ፖርቲ ድጋፍ ሰጥታለች በሚል ምክንያት ነበር ከቱርክ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገባችው።