ግብጽ የጋዛን ጦርነት ያቆማል ባለችው እቅድ ጉዳይ መልስ እየጠበቀች መሆኑን ገለጸች
የግብጽ ባለስልጣናት የእቅዱን ዝርዝሩ ከኳታር፣ ከእስራኤል፣ ከሀማስ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፖ መንግስታ ጋር ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ቢደረግም፣ እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ አልተቀበሉትም
ግብጽ የጋዛን ጦርነት ያስቆማል ባለችው እቅድ ጉዳይ መልስ እየጠበቀች መሆኑን ገልጻለች።
ግብጽ በትናንትናው እለት እንዳረጋገጠችው የጋዛን ጦርነት ያስቆማል ያለችውን በርካታ ምዕራፎች ያሉት እቅድ ማቅረቧን አረጋግጣለች።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ ካገኘች በኋላ ግብጹ የእቅዱን ዝርዝር እንደምታብራራ የግብጽ ስቴት ኢንፎርሜሽን ሰርቪስ ኃላፊ ዲያ ራሽዋን ተናግረዋል።
ኃላፊው የሁሉንም አካላት ሀሳብ በማቀራረብ የፍለስጤማውያንን ደም መፍስስ እና በጋዛ ሰርጥ ላይ የሚደረገውን ወረራ ለማስቆም የሚደረግ ሙከራ ነው ብለዋል።
ቀደምሲል የግብጽ የደህንነት ምንጮች እቅዱ የታጋቾች እና እስረኞች መልቀቅን የሚጠይቅ በርካታ ምዕራፎች ያሉት ተኩስ አቁምን እንደሚያካትት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
ከዚህ በተጨማሪም ግብጽ ጋዛና ዌስትባንክን የሚያስተዳድር የፍልስጤም መንግስት የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርባለች ተብሏል።
የግብጽ ባለስልጣናት የእቅዱን ዝርዝሩ ከኳታር፣ ከእስራኤል፣ ከሀማስ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፖ መንግስታ ጋር ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል።
እስራኤል ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በከፈተችው መጠነሰፊ ጥቃት ከ20ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ከተጀመረ ከ12 ሳምንታትን ያስቆጠረው ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ቢደረግም፣ እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ አልተቀበሉትም።