ግብፅ በአየር ድብደባ የወደሙ ህንጻዎችን ፍርስራሽ ለማንሳት ከባባድ የግንባታ መሳሪያዎችን ወደ ጋዛ ላከች
የግንበታ መሳሪያዎቹ በግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ ትእዛዝ ነው ወደ ጋዛ የገቡት
ለ11 ቀናት የቆየው የእስራኤል ሀማስ ግጭት የበርካቶችን ህይወት በመቅጠፍ በተኩስ አቁም ስምምነት መቋጨቱ ይታወሳል
ግብፅ በእስራኤል አየር አየር ድብደባ የወደሙ ህንጻች ፍርስራሽ ለማንሳት ከባባድ ግንባታ መሳሪያዎችን ወደ ጋዛ መላኳ ተሰምቷል።
የግንባታ መሳሪያዎቹ በጋዛ ሰርጥ በሚንቀሳቀሰው ሀማስ እና በእስራኤል መካካል በነበረ ግጭት የወደሙ ህንጻዎችን ፍርስራሽ ለማንሳት የሚውሉ መሆኑ ታውቋል።
የግብፅ የባህል ማእክል ዳይሬክተር አደል አብደልራህማን ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት፤ የግንበታ መሳሪያዎች በግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ ትእዛዝ ነው ወደ ጋዛ የገቡት።
ከግብጽ ወደ ጋዛ የተላኩት ከባድ ግንብታ መሳሪያዎቹ ውስጥም ከሬይኖች፣ ቡል ዶዘር እና በርከት ከባድ ተሸከርካሪዎች እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።
ወደ ጋዛ የገቡት ግንባታ መሳሪያዎቹ በእስራኤል አየር ድብደባ የወደሙ ህንጻዎች ፍርስራሽ ለማንሳት ይውላሉ ያሉ ሲሆን፤ ጋዛን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙም አስታውቀዋል።
በእስራኤል አየር ድብደባ የወደመችውን ጋዛ መልሶ ለመገንባትም ሁሉም ኢንጂነሮች እና የቴክኒክ ሰዎች ቀን ከሌት የሚሰሩ መሆኑንመ ነው አደል አብደልራህማን የተናሩት።
የእስራኤል እና በጋዛ የሚንቀሳቀሰው ሀማስ ግጭት ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ለ11 ቀናት ከቆየ በኋላ በሁለቱም ወገን የበርካቶችን ህይወት በመቅጠፍ በተኩስ አቁም ስምምነት መቋጨቱ አይዘነጋም።
በ11 ቀናቱ ውጊያም በፍልስጤም በኩል ቢያንስ የ232 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 65 ህጻናት እና 35 ሴቶች ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከ1 ሺህ 500 በላይ ፍልስቴማውያን ደግሞ መቁሰላቸውን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡
በእስራኤል በኩል ደግሞ የ12 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 2 ህጻናት ናቸው፤ ከ300 በላይ አስራኤላውያን ደግሞ ቆስለዋል።
በ11 የግጭቱ ቀናት ውስጥ ጋዛ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሀማስ ከ4 ሺህ በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል የተለያዩ ከተሞች መተኮሱን እስራኤል አስታውቃለች።
እስራኤልም በቀን በአማካኝ አስከ 100 የሚደርሱ የአየር ድብደባዎችን በጋዛ ሰርጥ ስትፈጽም የቆየች ሲሆን፤ ወደ ሊባናስም ከ100 በላይ መድፎችን መተኮሷ አይዘነጋም።