ግብጽ ምንምእንኳን ከአንድአንድ ወላጆች ተቃውሞ ቢነሳም ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዲቀመጡ ወስናለች
ግብጽ ምንምእንኳን ከአንድአንድ ወላጆች ተቃውሞ ቢነሳም ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዲቀመጡ ወስናለች
በግብጽ ምንምእንኳን ቫይረሱ እንዲስፋፋ እድል ይሰጣል ከሚሉ ከአንድአንድ ወላጆች ተቃውሞ ቢነሳም በ100ሺዎች የሚቆጠሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምክርት ቤት ተማሪዎች የአፍ ጭንብል (ማስክ)ና የእጅ ጓንት አድርገው ወደ ፈተና እያቀኑ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር 2500 አምቡላንሶችን አዘጋጅቷል፤ለእያንዳንዱ ትምህርትቤትም አንድ ዶክተር መመደቡን አስታውቋል፡፡ከፍተኛ ሙቀት ያሳዩ ተማሪዎች ፈተናቸው ለሌላ ጊዜ እንዲተላፍ ወይም ለብቻቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ተማሪዎች ፈተና ላይ ከመቀመጣቸው በፊት ጠዋት ሙቀታቸው እንደሚወሰድና ተራርቀው እንዲቀመጡ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡
በግብጽ በአጠቃላይ 670ሺ ተማሪዎች ከግልና ከመንግስትና 128ሺ ከሀይማኖታዊ ትምህርት ቤት ለፈተና ይቀመጣሉ፡፡ ሀገሪቱ ይህን ርምጃ የወሰደችው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በፍጥነት ጨምሮ 53ሺ በላይና የሟቾች ቁጥር ደግሞ 2106 በደረሰበት ወቅት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ምንምእንኳን የሀገሪቱ ባለስልጣናት በኮሮና ቫይረስ ተጥሎመ በነበረው የእንቅስቃሴ እግድ ላይ ቀስ በቀስ ቢያሉም ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ከባለፈው መጋቢት ጀምሮ ዝግ ሆነው ቆይተዋል፡፡
የግብጽ የህክምና ዶክተሮች ማህበር ኃላፊ ፈተናው እንዲራዘም መጠየቁን ሮይተርስ አልዮውም አልሳባ የተሰኘውን የግብጽ ጋዜጣ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ነገርግን ባለስልጣናቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፤ ትምህርት ሚኒስቴርም ፈተናውን ላለመውሰድ ለሚፈልግ ተማሪ ያለቅጣት የማራዘም እድል ይሰጣል ብለዋል፡፡