በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በትናንትናው እለት ብቻ 10 ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ ገልጿል
በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በትናንትናው እለት ብቻ 10 ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ ገልጿል
የሶማሌ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በሶማሌና በአፋር ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት የ27 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን አስታውቋል፡፡
ክልሉ እንደገለጸው በጠቅላላ የሞቱት 27 ሰዎች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 10ሩ በትናንትናው እለት በሲቲ ዞን የሞቱ መሆናቸው ገልጿል፡፡
“እንዲህ አይነት ድርጊት ተደጋጋሚ ከመሆናቸው እና የሰው ህይወት መጥፋት ከማሰከተላቸዉ በተጨማሪ ከባድ የንብረት ውድመቶች እያደረሱ ይገኛሉ”ያለው መግለጫው የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን ተጎጂዎችን ለመርዳት እሰራለሁ ብሏል፡፡
መግለጫው የአፋርና ሶማሌ ክልል ህዝቦች ወንድማማችነት እንዳይጎዳም ይሰራል ብላል፡፡
የክልሉ መንግስት የደረሰውን የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ወድሙትን በመመርመር መፍትሄ ለማምጣት ይሰራል፤የምርመራው ውጤትም ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብሏል መግለጫው፡፡
ሰለተፈጠረው ግጭት የአፋር ክልል እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
በአፋር ክልል የክሉሉ መንግስት አሸባሪ ባላቸው ሃይሎች ሁለት የትምህርት ሚኒስትር ሰራተኞችና ሌሎች መገደላቸውን ገልጾ ነበር፡፡
በሶማሊያ አፋር አዋሳኝ ቦታዎች ላይ የሚነሱ ግጭቶች ለመርካታ ንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ሲሆኑ ቆይተዋል፡፡