የምስራቅ ሽዋ ከፍተኛ ፍርድቤት አቶ ልደቱ በዋስ እንዲፈቱ ትእዛዝ የሰጠው ማክስኞ እለት ነበር
የምስራቅ ሽዋ ከፍተኛ ፍርድቤት አቶ ልደቱ በዋስ እንዲፈቱ ትእዛዝ የሰጠው ማክስኞ እለት ነበር
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ባወጣው መግለጫ አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ ትእዛዝ የሰጠላቸው እስረኞች ”በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል” ብሏል፡፡
“የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር” ነው ያለው መግለጫው የዋስትና ቅድመ ሁኔታ ያማሉ ታሳሪዎች ሊፈቱ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቢሾፍቱ አመጽ በማነሳሳት ተጠርጥረው ታስረው ነበር፡
ነገርግን ይህን የፖሊስ ክስ ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረገው በኋላ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተገኝቶባቸዋል በሚል ክስ ተከሰው የፍርድ ሂደታቸውም ወደ አዳም ምስራቅ ሽዋ ከፍተኛ ፍርድቤት እንዲዛወር ተደርጎ ሲከታተሉ ነበር፡፡
በቢሾፍቱ በነበረው የፍርድቤት ክርክር ጠበቆቻቸውን አሰናብተው የነበሩት አቶ ልደቱ የአዳማውን አዲስ ፍርድቤት ነው በማለት እንደገና በጠበቃ ሲከራከሩ ነበር፡፡
ፍርድቤቱ አቶ ልደቱ በ100ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ቢያዝም እስካሁን ፖሊስ የፍርድቤቱን ትእዛዝ ተቀብሎ ፖለቲከኛውን ልደቱን አልፈታቸውም፡፡
አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ በዋስ ቢወጡ ውጭ የህክምና ቀጠሮ ስላላቸው ሄደው ይቀሩብኛል በሚል ያቀረበው መከራከሪያ የዋስትና ገንዘቡ ከፍ እንዲል ምክንያት እንደሆነ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዘዳንት (ኢዴፓ) አቶ አዳነ ባለፈው ማክሰኞ ለአል አይን አማርኛ ገልጸው ነበር፡፡
የአቶ ልደቱ የዋስትና መብት በ2/3 የዳኞች ድምጽ መጽደቁንም አቶ አዳነ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ገዳዩን እየተከታተሉት ያሉት አቶ አዳነ ዛሬም ችሎት መቅረባቸውንና ዳኛው“ነገ እንናሳውቃችኋለን” ማለታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈዋል፡፡
አቶ ልደቱ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድቤቱ የወሰነው ባለፈው ማክሰኞ ነበር፡፡