የምክርቤት አባላትን ጨምሮ በአዋሽ አርባ የታሰሩ 53 ሰዎችን መጎብኘቱን ኢሰመኮ ገለጸ
ኢሰመኮ ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር አደረኩት ባለው ውይይት በእሰረኞች ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ጥሰቶች እንዲጣሩ እና ታሳሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገኛኙ እንዲደረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል
ኢሰመኮ እንደገለጸው አዋሽ አርባ ከፍኛ ሙቀት ያለበት መሆኑ እና መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ባለመሆኑ ለህይወታቸውን እንደሚሰጉ መግለጻቸውን ኢሰመኮ ገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኙትን በትናንትናው እለት መጎብኘቱን ገልጿል።
ታሳሪዎቹ የተወካዮች ምክርቤት አባላት እና ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
ኢሰመኮ በሪፖርቱ "ታሳሪዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤ እንዲሁም ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤ እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች" መሆናቸውን ገልጿል።
እነዚህ ታሳሪዎች "ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ/መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡" ብሏል ኢሰመኮ።
ታሳሪዎቹ ወደ አዋሽ አርባ መውሰድ ያስፈለገበት ምክንያት በአዲስ አበባ ያለው የፌደራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ በመጣበቡ በመሆኑን ፖሊስ እንዳስረዳው ኢሰመኮ ጠቅሷል።
ፖሊስ የታሳሪዎቹ አያያዝ ሰብአዊ መብትን ያከበረ መሆኑን፣ ህክምና እንዲያገኙ ማደረጉን እና ቤተሰባቸውን እንዲያገኙ እንደሚያመቻች መግለጹን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ገልጿል።
ነገርግን "እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ፣ ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው"ኢሰመኮ በሪፖርቱ ጠቅሷል።
ከታሳሪዎቹ መካከል ከአማራ ክልል የመጡት ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን ኢሰመኮ ገልጿል።
ኢሰመኮ እንደገለጸው ታሳሪዎቹ አዋሽ አርባ ከተፍኛ ሙቀት ያለበት መሆኑ እና መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ባለመሆኑ ለህይወታቸው እንደሚሰጉ መግለጻቸውን ኢሰመኮ ገልጿል።
ኢሰመኮ ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር አደረኩት ባለው ውይይት በእሰረኞች ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶች እንዲጣሩ እና ታሳሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገኛኙ እንዲደረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።
ኢሰመኮ በኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ ከመታሩት ውጭ "በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፤ በአማራ ክልል ደብረ ታቦር፣ ባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች፤ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በገላን እና በሸገር እንዲሁም ሌሎች ከተሞች፣ መደበኛ ያልሆኑ ቦታዎች ተይዘው" ከነበሩት ውስጥ ከፊሎቹ የተቀቀሉ ሲሆኑን ከፊሎቹ አለመቀቃቸውን ገልጿል።
መንግስት በአማራ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር ያባብሳሉ በሚል ምክንያት ነበር እነዚህን ግለሰቦች ያሰረው።