የዘንድሮው ኢድ አል አድሃ በዓል መቼ ይከበራል?
የ2024 የሀጂ ጉዞ ከሰኔ 1 እስከ 6 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
ኢድ አል አድሃ በዓል በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ይከበራል
የዘንድሮው ኢድ አል አድሃ በዓል መቼ ይከበራል?
በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የኢድ አል አድሃ በዓል የፊታችን ሰኔ ወር ይከበራል ተብሏል፡፡
አል አረቢያ እንደዘገበው ከሆነ የዘንድሮው ኢድ አል አድሃ በዓል ሰኔ ዘጠኝ ቀን 2016 ዓ.ም ይከበራል ተብሏል፡፡
በዕምነቱ ተከታዮች ዘንድ እንደ ቅዱስ ስፍራ የምትታየው መካ ደግሞ በዓሉ በድምቀት የሚከበርባት ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራው ያመራሉ፡፡
የዘንድሮው የሀጂ ጉዞም ከሰኔ 1 እስከ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የሀጂ በዓል ደግሞ ሰኔ 7 ቀን በመካ ይከበራል ተብሏል፡፡
በመቀጠልም የኢድ አል አድሃ በዓል ደግሞ ከሰኔ 15 ጀምሮ እንደሚከበር ሳውዲ አረቢያ አስታውቃለች፡፡
የኢድ አል አድሃ በዓል በተለያዩ ሁነቶች የሚከበር በዓል ሲሆን በተለይም አቅም የሌላቸውን በመርዳት፣ ፈጣሪን በማመስገን እና በጸሎት ይከበራልም ተብሏል፡፡
ሳኡዲ አረቢያ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ በተፈቀደ ስፍራ ገብቶ የተገኘ ጋዜጠኛን አሰረች
የእስልምና ዕምነት በምድር ላይ ህይወቱ አንድ ጊዜ በመካ ተገኝቶ ፈጣሪን የማመስገን ፍላጎት እንዳለው ሲገለጽ ሳውዲ አረቢያም በየዓመቱ ለሀጂ ተጓዦች በመላው ዓለም ለሚገኙ የእስልምና ተከታዮች የጉብኝት እድል ትሰጣለች፡፡
በዚህ የሀጂ ጉዞ መሰረትም ወደ መካ የሚመጡ የእስልምና ተከታዮች በመብዛታቸው ምክንያት በመረጋገጥ እና ድካም ምክንት ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በተካሄደው የሀጂ በዓል ወቅት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎች ወደ ሳውዲ የተጓዙ ሲሆን በሙቀት እና መገፋፋት ምክንያት ከ230 በላይ ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡