ልዩልዩ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት የግብጽ እስልምና ኢንስቲትዩት ያወጣውን መግለጫ ተቃወመ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል
አልአዝሀር የተሰኘው የግብጽ እስልምና ኢንስቲትዩት ሙስሊሞች የህዳሴውን ግድብ እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርቦ ነበር
አልአዝሀር ኢንስቲትዩት ከቀናት በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ ትክክል አይደለም፤ ወንዙ የሁላችንም በመሆኑ ሁሉም ሰው ሊቃወመው ይገባል ሲል መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
ኢንስቲትዩቱ አክሎም ግድቡ ግብጽ እና ሱዳን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ አረቦች እና ሙስሊሞች ሁሉ እንዲቃወሙት ሲል ጥሪ አቅርቦ ነበር።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ አልአዝሀር የተሰኘው የግብጽ እስልምና ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለው የህዳሴ ግድብ የግብጽን እና ሱዳንን ህዝብ ለችግር ይዳርጋል ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብሏል።
ግብጽና እና ሱዳን አባይ ወንዝን እስከዛሬ እንደፈለጉ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፤አሁን ኢትይጵያ እያለች ያለችው ሁላችንም በፍትሀዊነት እንጠቀምበት በመሆኑ አልአዝሀር ያወጣው መግለጫ ተቀባይነት የለውም ሲል ምክር ቤቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማድረግ መዘጋጀቷን በተደጋጋሚ አስታውቃለች፡፡