ታዋቂው የእስልምና ምሁር ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ዩሱፍ አል ቃራዳዊ ዓለም አቀፍ የሙስሊም ምሁርና ተሟጋች ነበሩ
ዩሱፍ አል ቃራዳዊ ከግብጹ የሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ይነገራል
ታዋቂው የእስልምና ምሁር ዩሱፍ አል ቃራዳዊ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን አለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ህብረት አስታወቀ።
ሼክ ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸውበዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ህብረቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ታዋቂው የእስልምና ምሁር ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በፈረንጆቹ 2004 የተቋቋመውን አለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽንን ከተቋቋመበተ ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።
ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በሰሜናዊ ግብጽ በምትገኘው ግራሃቢ ግዛት የተወለዱ ሲሆን፤ ኑሯቸውን ግን በኳታር ነው ያደረጉት።
ከግብጹ የሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚነገረው ዩሱፍ አል ቃራዳዊ፤ የኳታር ዜግነት ተሰጥቷቸው ህይወታቸው እስክታለፍ ድረስ ኑሯቸውን በዶሃ ነበር የኖሩት።
ዕውቁ የእስልምና ምሁር ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በክፈለ ዘመኑ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ ነበሩ።