1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል
በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ ዛሬ ምሽት ላይ ባደረገው ምልከታ አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ ኢድ ከነገ በስቲያ ይሆናል
ህዝበ ሙስሊሙ ባለፉት 29 ቀናት የረመዳን ጾም ሲጾም ቆይቷል
1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።
በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር 29ኛው ቀን ጀንበር ከጠለቀች በኋላ የጨረቃ ምልከታ ያደረገ ሲሆን፥ በዚህም ምሽት ላይ አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ ኢድ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ሚያዚያ 2 2016 ይሆናል ብሏል።
የኢድ አልፈጥር የመጀመሪያ ቀን የሚወሰነው በሂጅራ አቆጣጠር 10ኛው ወር ወይም ሸዋል ወር መጀመሩን የሚያመላክት ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ነው።
ህዝበ ሙስሊሙ ባለፉት 29 ቀናት የረመዳን ጾም ሲጾም ቆይቷል።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና የመከባበሪያ ወር ነው።
ሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፉት 29 ቀናት ፈጣሪ የሚወደውን በጎ ተግባራት በማከናወን በጾምና በጸሎት አሳልፏል። ኢድ ከነገ በስቲያ በመሆኑም ዘንድሮ ጾሙ ለ30 ቀናት ይቆያል።
አስተምህሮ ያዛል።የኢድ አል ፈጥር በዓል እንዴት ይከበራል?
የኢድ አል ፈጥር በዓል የእስልምና እምነተ ተከታይ በሚበዙባቸው ሀገራት በተለምዶ ለሶስተ ቀና የሚከበር ሲሆን፤ እንደየ ሀገራቱ የበዓላቱ ቀናት ቁጥር ሊለያይ ይችላል።
ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ ቀን አከባበርን የሚጀመረው ጎህ ሲቀድ በሚደረገው የጋራ የሰላት ስነስርዓት ላይ በመሳተፍ ነው።
ህዝበ ሙስሊሙ የጋራ ሰላት ወደ ሚደረግበት ስፍራ በጋራ ሲሄዱም “አላሁ አክበር” በማለት ተክቢራትን እያሰሙ ለፈጣሪ ምስጋና እያቀረቡ ነው።
ይህ ልዩ በዓል “ጣፋጭ” ኢድ በመባል በብዛት የሚታወቅ ሲሆን፤ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ከኢድ ከሶላት በፊት ጣፋጭ መብላት የተለመደ ነው።
በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች ከቴምር እና ሌሎች ጣፋጭ ነገሮች የተሰሩ ማሙል በመባል የሚታወቁ ብስኩቶችን መመገብ የተለመደ ተግር ነው።
በአብዛኞቹ ሀገራት አብዛኛውን ጊዜ ሙስሊሞች የኢድ ቀንን ጣፋጭ ነገሮችን በመያዝ ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ዘመዶቻቸውን እና ጎረቤቶቻቸውን በመጠየቅ ያሳልፋሉ።
ህጻናት ልጆችም አዲስ ልብስ ለብሰው ስጦታ እየተቀበሉ በዓሉን ተደስተው ያሳልፋሉ።
በኢድ አል ፈጥር እለት ሰዎች የበዓል መልካ ምኞት መግለጫዎቻቸውን በተለያየ መልኩ የሚገልጹ ሲሆን፤ በብዛት በጥቅም ላይ ከሚውሉት የመልካም ምኞት መግለጫዎች ውስጥ ግን "ኢድ ሙባረክ" (የተባረከ ኢድ) ወይም "ኢድ ሰኢድ" (መልካም ኢድ) የሚሉት ተወዳጅና በስፋት ጥምቅ ላይ የሚውሉ ናቸው።