የኢድ ሰላት በመላው ኢትዮጵያ በምስል
1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ነው
ህዝበ ሙስሊሙ የጋራ የሰላት ስነስርዓት በማከናወን በዓሉን ማክበር ጀምሯል
የታላቁ የረመዳን ጾም ወር ወደ መጠናቀቁን ተከትሎ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ አል ፈጥር በዓልን እያከበሩ ነው።
1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት እየተከበረ ይገኛል።
ህዝበ ሙስሊሙ ከማለዳ ጀምሮ የጋራ የሰላት ስነስርዓት ወደሚያከናውንባቸው ሰፊ ስፍራዎችን አቅንቷል።
የሰላት ስነስርአቱ በአዲስ አበባ፣ ሀረር፣ ጋምቤላ፣ መቱ፣ ከሚሴ እና ሌሎች ከተሞች በድምቀት ተከብሯል።
ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያገኘናቸውን የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ምስሎች ይመልከቱ፦