ልዩልዩ
የአለም መሪዎች ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ቢሆኑ ምን ይመስላሉ?
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እገዛ የተሰሩት ታዋቂ የሀገራት መሪዎች ቅርጫት ኳስ ሲጫወቱ የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ትኩረት ስበዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጨዋታ መሀል ሸለብ አድርጓቸው ይታያሉ
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ቴክኖሎጂዎች መረጃን በመስጠት ብቻ ምስልና ቪዲዮ መስራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
ቴክኖሎጂውን የተጠቀመ አንድ ግለሰብም የሀገራት መሪዎች የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ቢሆኑ ምን እንደሚመስሉ የሚያሳዩ ምስሎችን ለቆ ትኩረት ስቧል።
ምስሎቹ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የህዳር ወር ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን፣ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የቻይናው ፕሬዝዳን ሺ ጂንፒንግ ቅርጫት ኳስ ሲጫወቱ ያሳያሉ።
በተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች ሲተኙ የታዩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጨዋታ መሀል ሸለብ አድርጓቸው የሚያሳየው ምስልም እያነጋገረ ነው።
የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ቢሆኑ ምን እንደሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምስል ከተሰራለቸው መካከል ይገኙበታል።