በራፋ 8 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ጦሩ አስታወቀ
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ወታራዊ ክንፍ ተሽከርካሪው የተጠመደ ፈንጅ ወስጥ መግባቱን እና ፍንዳታው መፈጠሩን ገልጿል
የእስራኤል ጦር በራፋ ከተማ የሚያደርገውን ጥቃት እያጠናከረ ባለበት ወቅት ስምንት የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ጦሩ አስታውቋል
በራፋ እየተካሄደ ያለው ውጊያ ሲቀጥል 8 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ጦሩ ተገድለዋል።
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ባለችው የራፋ ከተማ ውስጥ እና ዙሪያ የሚያደርገውን ጥቃት እያጠናከረ ባለበት ወቅት ስምንት የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ጦሩ አስታውቋል።
ጦሩ እንደገለጸው የተገደሉት ወታደሮች የኢንጂነሪንግ ቡድን አባለት መሆናቸውን እና በተሳፈሩበት ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ላይ ተጭኖ የነበረው ቁስ ሲመታ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነው።
በምዕራብ ራፋ ቴል አል ሱልጣን የተፈጠረው ክስተት እየተመረመረ ነው ብሏል ጦሩ።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ወታራዊ ክንፍ ተሽከርካሪው የተጠመደ ፈንጅ ውስጥ መግባቱን እና ፍንዳታው መፈጠሩን ገልጿል።
የእስራኤል ታንኮች በቴል አል ሱልጣን እየገፉ እና ለበርካታ ጊዜ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን የተጠለሉበትን ጠረፋማ ቦታዎች እየደበደቡ ናቸው።
ስምንት ወራትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ወደ ተኩስ አቁም እንዲያመራ አለምአቀፍ ጫና ቢደረግም እስካሁን አልተሳካም። በቀጠለው የእስራኤል ጥቃት በጋዛ ከተማ ዳርቻዎች ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች ተጨማሪ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ሮይተርስ የጤና ባለሙያዎች ጠቅሶ ዘግቧል።
እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ እለት ጦሯ በግብጽ ድንበር በምትገኘው ራፋ በመሬት ላይ እና በሃማሴን በተሰሩ ቱቦዎች ውስጥ ተደብቀው የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መያዙን አስታውቃለች።
ጦሩ የሀማስ ታጣቂዎች የሰብአዊ አገልግሎት ቀጣና ከሆነው የማዕከላዊ ጋዛ ክፍል አምስት ሮኬቶችን ባለፈው ሳምንት አርብ እንደተኮሱበትም ገልጿል።
ጦሩ ይህ ሀማስ የሰብአዊ አገልግሎት መሰጫ መሰረተልማቶችን ለመበዝበዝ እና ንጹሃንን እንደ ጋሻ ለመጠቀም ያለውን ሴራ የሚያሳይ ነው ሲል ከሷል።
የስምንቱ ወታደሮች ሞት የሀመል ፓለቲካ አራማጁ የቀድሞ ጀነራል ቤን ጋንዝ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ያጋጠማቸውን የፓለቲካ ቀውስ ያባብሳል ተብሏል።
ሀማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፍቶ 153 ሰዎች ካገተ እና 1200 የሚሆኑትን ከገደለ በኋላ እስራኤል እየወሰደች ባለው የአጸፋ እርምጃ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ37ሺ ማለፉን የጋዛ ጤና ባለስልጣናት ይገልጻሉ።