የእስራኤል ጦር 4 ታጋቾችን በህይወት ማስለቀቁን አስታወቀ
አራቱ እስራኤላውያን የታገቱት ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በደቡባዊ እስራኤል በኖቫ በተካሄደው የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ነበር።
እነዚህ እስራኤላውያን አሁን ላይ በትጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን እና ለተጨማሪ የህክምና ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላካቸውን ጦሩ ገልጿል
የእስራኤል ጦር 4 ታጋቾችን በህይወት ማስለቀቁን አስታወቀ።
አራት እስራኤላውያን ታጋቾችን ከሀማስ እጅ በህይወት ማስለቀቁን የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት አስታውቋል።
ጦሩ ባወጣው መግለጫ ናኣ አርጋማኒ፣ አልሞግ ሚየር ጃን፣ አንድሪ ኮዝሎቭ፣ ሽሎሚ ዚቭ የተባሉ ታጋቾችን በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኑሲራት የተለያዩ ቦታዎች ከእነህይወታቸው ማግኘት ችሏል።
እነዚህ እስራኤላውያን አሁን ላይ በትጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን እና ለተጨማሪ የህክምና ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላካቸውን ጦሩ ገልጿል።
አራቱ እስራኤላውያን የታገቱት ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በደቡባዊ እስራኤል በኖቫ በተካሄደው የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ነበር።
አርጋማኒ፣ የሀማስ ታጣቂዎች ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ በሞተርሳይክል ይዘዋት ሲሄዱ በቪዲዮ ታይታለች። የእስራኤል መንግስት ሀማስ ባለፈው የፈረንጆቹ ጥቅምት ሰባት ባደረሰው ጥቃት 252 ሰዎችን ሳያግት እንዳልቀረ ግምቱን አስቀምጧል። ባለፈው አመት ከሀማስ ጋር በተደረጉ ድርድሮች 112 የሚሆኑት ተለቀዋል። አሁን ላይ 80 ታጋቾች በሀማስ እጅ አሉ ተብሎ ይገመታል።
ሀማስ ባደረሰባት ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገባችው እስራኤል የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ መጠነሰፊ የአየር እና የእግረኛ ጦር ጥቃት እያደረሰች ነው።
የእስራኤል ጦር በአሁኑ ወቅት የሀማስ የመጨረሻ ምሽግ ይገኝባታል የተባለችውን የራፋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ጥቃት ከፍቷል፤ በጋዛ በኩል ያለውን የራፋ ድንበርም ቀደም ሲል ተቆጣጥሮታል።
እንደ ጋዛ የጤና ባለስልጣናት ከሆነ እስራኤል እስካሁን በወሰደችው ጥቃት ከ36ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።