በቪንሺየስ ጁኒየር ላይ የዘረኝነት ትንኮሳ የፈጸሙ ሶስት ደጋፊዎች በእስራት ተቀጡ
በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን ያመኑት ደጋፊዎች ለሁለት አመታት ያህል ወደ ስቴዲየም እንዳይገቡ እግድ ተጥሎባቸዋል
የላሊጋ ፕሬዝደንት ውሳኔው በስፔን ውስጥ ያለውን ዘረኝነት ለመዋጋት እና በቪንሺየስ ጁኒየር ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የሚጠቅም ጥሩ ዜና ነው ሲሉ አወድሰውታል
በቪንሺየስ ጁኒየር ላይ የዘረኝነት ትንኮሳ የፈጸሙ ሶስት ደጋፊዎች በእስራት ተቀጡ።
ሶስት የቫሌንሺያ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በቪንሺየስ ጁኒየር ላይ በሰነዘሩት የጥላቻ ስድብ የስምንት ወራት እስራት እንደተፈረደባቸው እና ይህም በሰፔን በስቴዲየም ውስጥ ለተፈጸመ የዘረኝነት ስድብ የተላለፈ የመጀመሪያው ፍርድ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
ፍርድ ቤቱ ባወጣው መግለጫ " ዛሬ በተላለፈው የመጨረሻ ውሳኔ፣ ሶስቱ ተከሳሾች ቪንሺየስ ጁኒየርን በመጮህ፣ የቆዳ ቀለሙን በመጥቀስ ምልክት በማሳየት መስደባቸው ተረጋግጧል" ብሏል።
"እነዚህ ጩኸቶች እና ሲያሳዩቸው የነበሩት ምልክቶች በባህሪያቸው ዘረኛ እንዲሁም የዝንጀሮ እንቅስቃሴ እና ጩኸት ያካተቱ ስለነበሩ ተጨዌቹ እንዲሸማቀቅ እና ብሎም ተፈጥሮአዋ ክብሩ እንዲነካ አድርገዋል" ብሏል ፍርድ ቤቱ።
በስፔን ህግ መሰረት ከሁለት አመት በታች እስር የተላለፈባቸው ፍርደኞች የኋላ የወንጀል ታሪክ ከሌላቸው በእስር እንዲቆዩ ላይገደዱ ይችላሉ፤ ስለዚህ እነዚህ ሶሰት ፍርደኞችም ሊለቀቁ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን ያመኑት ደጋፊዎች ለሁለት አመታት ያህል ወደ ስቴዲየም እንዳይገቡ እግድ ተጥሎባቸዋል።
የላሊጋ ፕሬዝደንት ጃቪየር ቴባስ ውሳኔው በስፔን ውስጥ ያለውን ዘረኝነት ለመዋጋት እና በቪንሺየስ ጁኒየር ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የሚጠቅም ጥሩ ዜና ነው ሲሉ አወድሰውታል።
በቪንሺየስ ላይ የዘረኝነት ስድብ የተወረወረበት ባለፈው አመት ግንቦት ወር በቫሌንሺያው ማስታላ ስቴዲየም በተካሄደ የሊግ ጨዋታ ላይ ነበር። ይህን ተከትሎ ብራዚላዊው አጥቂ አለም አቀፍ ድጋር የጎረፈለት ሲሆን ድርጊቱን የሚቃወሙ ሀገራዊ አለምአቀፋዊ ዘመቻዎችም ተከፍተው ነበር። ቪንሺየስ ላይ የደረሰው ትንኮሳ አለምአቀፉ የእግር ኳስ አካል ፊፋ ጸረ-ዘረኛ የሆነ የተጨዋቾች ቡድን እንዲያቋቁም ምክንያት ሆኗል።
የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ደጋፊዎች በፍርድ ቤት በንባብ ባሰሙት ንግግር ቪንሺየስ ጁኒየርን፣ ላሊጋን እና ሪያል ማድሪድን ይቅርታ ጠይቀዋል ተብሏል።
ሪያል ማድሪድ ተከሳሾቹ መጸጸታቸውን እና ምንም አይነት ዘረኝነት እንዲያስወግዱ ለደጋፋዎች መልእከት አስተላልፈዋል ብሏል።