በሱዳን በትናንቱ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 8 ደረሰ
በሱዳን በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 111 ደርሷል
6 ሰዎች በኦምዱርማን፤ 2 ሰዎች በካርቱም በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል
ሱዳናውያን በትናንትናው እለት ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ባደረጉት ጉዙፍ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ስምንት ደረሰ።
ትናንት በሱዳን የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ የጠሩት የሀገሪቱ ተቃዋሚ ኃይሎች የጠሩት ሲሆን፤ የሰልፉ ዋነኛ አላማም ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣንን ወደ ሲቪል እንዲያሸጋግር ለመጠየቅ ነው ተብሏል።
የሱዳን ጦር ሠራዊት መሪ ብ/ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን በህዳር ወር ውስጥ በመፈንቅለ መንግሥት የተቆጣጠሩትን ሥልጣን እንዲያስረክቡ ሰልፈኞች ጠይቀዋል።
ሀገሪቱ የተጠራውን ግዙፍ ሰልፍ ተከትሎ የካርቱም የፀጥታ ኃይሎች እና ወታደራዊ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን፤ በዚህም ንጹሃን መሞታቸው ተነግሯል።
የሱን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መረጃ በኦምዱርማን እና በካርቱም ከተሞች በተካሄደው ሰልፍ ላይ ስምንት ሰዎች ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትው መሞታው ተነግሯል።
መንግስታዊ ያልሆነው ይህ የዶክተሮች ኮሚቴ በሰጠው መግለጫው፤ ለጊዜው ማንነታቸው ያልተለየው ሰልፈኞች ደረታቸው እና ጭንቅላት ላይ በጥይት ተመትተው መሞታቸውን አስታውቋል።
በተጨማሪም በካርቱም፣ በኦምዱርማ እና ባህሪ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ላይ በርካታ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፈኞች መጎዳታቸውን የሚያሳይ ሪፖርት እንደደረሰውም ኮሚቴው አስታውቋል።
በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ዛሬውን ጨምሮ 111 ደርሷል።
የሱዳን ጦር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላህ ሀምዶክን ከስልጣን በማውረድ ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያቶች የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
በሱዳን ከተካሄደው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደገባች ይታወሳል።
በቅርቡ ስዳናውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያስችናል ያትን ንግግር ቢጀምሩም የአፍሪካ ህረት ግለጸኝነት ይጎድለዋል በሚል ራሱን ከድርድር ሂደቱ ማግለሉ ይታወሳል።