በሱዳን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የቡርሃን መንግሥት ይውደም” የሚሉና ሌሎችም መልእክቶች ተሰምተዋል
ሱዳናውያን በዛሬው እለት ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ጉዙፍ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የተቃውሞ ሰልፉን የሱዳን ተቃዋሚ ኃይሎች የጠሩት ሲሆን፤ የሰልፉ ዋነኛ አላማም ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣንን ወደ ሲቪል እንዲያሸጋግር ለመጠየቅ ነው ተብሏል።
የሱዳን ጦር ሠራዊት መሪ ብ/ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን በህዳር ወር ውስጥ በመፈንቅለ መንግሥት የተቆጣጠሩትን ሥልጣን እንዲያስረክቡ ሰልፈኞች ጠይቀዋል።
“የቡርሃን መንግሥት ይውደም” የሚሉ እና ሌሎችም ወታራዊ መንግስቱን የሚቃወሙ መፈክሮችም በሰልፎቹ ላይ ተስትውለዋል።
ሀገሪቱ የተጠራውን ግዙፍ ሰልፍ ተከትሎ የካርቱም የፀጥታ ኃይሎች እና ወታደራዊ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል።
የሱን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መረጃ በኦምዱርማን ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ አራት ሰዎች ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትው መሞታው ተነግሯል።
መንግስታዊ ያልሆነው ይህ የዶክተሮች ኮሚቴ በሰጠው መግለጫው፤ ለጊዜው ማንነታቸው ያልተለየው ሰልፈኞች ደረታቸው እና ጭንቅላት ላይ በጥይት ተመትተው መሞታቸውን አስታውቋል።
በተጨማሪም በካርቱም፣ በኦምዱርማ እና ባህሪ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ላይ በርካታ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፈኞች መጎዳታቸውን የሚያሳይ ሪፖርት እንደደረሰውም ኮሚቴው አስታውቋል።
በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ዛሬውን ጨምሮ 107 ደርሷል።
የሱዳን ጦር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላህ ሀምዶክን ከስልጣን በማውረድ ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያቶች የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
በሱዳን ከተካሄደው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደገባች ይታወሳል።
በቅርቡ ስዳናውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያስችናል ያትን ንግግር ቢጀምሩም የአፍሪካ ህረት ግለጸኝነት ይጎድለዋል በሚል ራሱን ከድርድር ሂደቱ ማግለሉ ይታወሳል።