ስፖርት
በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ ሀገራት
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ጨዋታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ ስምንት ሀገራት ተለይተዋል
የሩብ ፍጻሜ ውድድሮች በሚቀጥለው አርብ መካሄድ ይጀምራሉ
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ጨዋታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ ስምንት ሀገራት ተለይተዋል።
ናይጀሪያ፣አንጎላ፣ ዲአር ኮኔጎ፣ ጊኒ፣ኬፕቨርዴ፣ ኮትዲቮር፣ማሊና እና ደቡብ አፍሪካ ወደ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታው አልፈዋል።
የዘንድሮው ውድድር ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል።የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በኳስ በብዙዎች ዘንድ ያልተጠቁ ውጤቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
በውድድሩ ረጅም ርቀት ይሄዳሉ የሚል ግምት የተሰጣቸው ሞሮኮ፣ የውድድሩ 2019 አሸናፊዋ አልጀሪያ፣ የ2021 አሸናፊዋ ሴኔጋል፣ አልጀሪያ እና ጋና ከሩብ ፍጻሜው በፊት ተንጠባጥበዋል።
የሩብ ፍጻሜ ውድድሮች በሚቀጥለው አርብ መካሄድ ይጀምራሉ።