በሶማሊያ በተፈጠረ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የ29 ሰዎች ሕይወት አለፈ
ኤልኒኖ የተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ 300 ሺህ ሶማሊዊያንን ከቤታቸው አፈናቅሏል
ኢትዮጵያ እና ኬንያም በዚሁ ጎርፍ ተጎድተዋል ተብሏል
በሶማሊያ በተፈጠረ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የ29 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ በተከሰተ የውሃ መጥለቅለቅ የ29 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
በአካባቢው የተከሰተው የውሃ መጥለቅለቅ የአየር ንብረት ለውጥ ውጤት ነው የተባለ ሲሆን በተለይም ኤልኒኖ የተሰኘው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የውሃ መጥለቅለቅ አደጋ አካል ነው ተብሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምስራቅ ኢትዮጵያ በተለይም ሶማሊ ክልል ፣ሶማሊያ እና ኬንያ በተከሰተ ከባድ ዝናብ በዜጎች ላይ ጉዳት አስከትሏል፤፡
በዚህ አደጋ ከ30 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ300 ሺህ በላይ ያህሉ ደግሞ በውሃው መጥለቅለቅ ምክንት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
መሰል የውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ሲያጋጥም በ40 ዓመት ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የሶማሊያ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ ሃላፊ ሞሃመድ ሞዓሊም እንዳሉት አደጋው ሊደርስ እንደሚችል አስቀድመን አስጠንቅቀን ነበር ነገር ግን የተፈጠረው ሆነ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ደቡባዊ ሶማሊያ በውሃ መጥለቅለቁ አደጋ ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን በግጭት እና አለመረጋጋት ሲሰቃይ ለነበረው 17 ሚሊዮን ህዝብ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ አደጋ ሊጋለጥ ችሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በጎርፉ ምክንያት ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ መቸገሩን ገልጿል፡፡
2 ሺህ 400 ዜጎች በከፍተኛ ጎርፍ አደጋ ውስጥ ተከበው እንደሚኖሩ የገለጸው ድርጅቱ በተለይም ሉቅ ከተማ ክፉኛ እንደተጎዳች አስታውቋል፡፡
አሁን የተከሰተው የኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ እስከ ቀጣዩ ዓመት ሚያዚያ ወር ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡
በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ እየቀነሰ ነው ተባለ
የአሁኑ አደጋ ከሶማሊያ በጠጨማሪ በኬንያ እና ኢትዮጵያም ተመሳሳይ አደጋ ያደረሰ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ከ35 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ12 ሺህ በላይ ደግሞ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
በፈረንጆቹ 1997 ላይ በምስራቅ አፍሪካ አምስት ሀገራት በኤልኒኖ አደጋ ምክንያት 6 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተው ነበር ተብሏል፡፡
ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 800 ያህሉ ሶማሊዊያን ሲሆኑ በ2006 ዓመት በተመሳሳይ በተከሰተ አደጋ 140 ሶማሊዊያን ህይወታቸውን አጥተውም ነበር፡፡